Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 8:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ከክ​ፉ​ዎች አጋ​ን​ን​ትና ከደ​ዌ​ያ​ቸው ያዳ​ና​ቸው ሴቶ​ችም አብ​ረ​ውት ነበሩ። እነ​ር​ሱም፦ መግ​ደ​ላ​ዊት የም​ት​ባ​ለው ሰባት አጋ​ን​ንት የወ​ጡ​ላት ማር​ያም፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እንዲሁም ከርኩሳን መናፍስትና ከደዌ የተፈወሱ አንዳንድ ሴቶች ዐብረውት ነበሩ፤ እነርሱም ሰባት አጋንንት የወጡላት መግደላዊት የተባለችው ማርያም፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ከክፉዎች መናፍስትና ከደዌም ተፈውሰው የነበሩ አንዳንድ ሴቶች፤ ከእነርሱም፦ ሰባት አጋንንት የወጡላት መግደላዊት የምትባል ማርያም፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እንዲሁም ከርኩሳን መናፍስት የተላቀቁና ከበሽታ የተፈወሱ ሴቶች ኢየሱስን ይከተሉት ነበር፤ እነርሱም ሰባት አጋንንት የወጡላት መግደላዊት የተባለችው ማርያም፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 አሥራ ሁለቱም ከእርሱ ጋር ነበሩ፥ ከክፉዎች መናፍስትና ከደዌም ተፈውሰው የነበሩ አንዳንድ ሴቶች፤ እነርሱም ሰባት አጋንንት የወጡላት መግደላዊት የምትባል ማርያም፥

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 8:2
11 Referencias Cruzadas  

ከሳምንቱም በመጀመሪያው ቀን ማልዶ በተነሣ ጊዜ፥ አስቀድሞ ሰባት አጋንንት ላወጣላት ለመግደላዊት ማርያም ታየ።


በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ መስ​ቀል አጠ​ገ​ብም እናቱ፥ የእ​ና​ቱም እኅት፥ የቀ​ለ​ዮ​ጳም ሚስት ማር​ያም፥ መግ​ደ​ላ​ዊት ማር​ያ​ምም ቆመው ነበር።


እነ​ዚህ ሁሉ ከሴ​ቶ​ችና ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ እናት ከማ​ር​ያም፥ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቹም ጋር በአ​ን​ድ​ነት ለጸ​ሎት ይተጉ ነበር።


ከገ​ሊ​ላም ከእ​ርሱ ጋር የመጡ ሁለት ሴቶች ተከ​ት​ለው፥ መቃ​ብ​ሩን፥ ሥጋ​ው​ንም እን​ዴት እን​ዳ​ኖ​ሩት አዩ። ተመ​ል​ሰ​ውም ሽቱና ዘይት አዘ​ጋጁ፤ ነገር ግን በሰ​ን​በት አል​ሄ​ዱም፤ ሕጋ​ቸው እን​ዲህ ነበ​ርና።


የሚ​ያ​ው​ቁት ሁሉና ከገ​ሊላ ጀምሮ የተ​ከ​ተ​ሉ​ትም ሴቶች በሩቁ ቆመው ይህን ያዩ ነበር።


ብዙ ሰዎ​ችም ተከ​ተ​ሉት፤ ሴቶ​ችም “ዋይ ዋይ” እያሉ ያዝ​ኑ​ለ​ትና ያለ​ቅ​ሱ​ለት ነበሩ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ስምህ ማነው?” ብሎ ጠየ​ቀው፤ እር​ሱም፥ “ስሜ ሌጌ​ዎን ነው” አለው፤ ብዙ አጋ​ን​ንት ይዘ​ውት ነበ​ርና።


ሰንበትም ካለፈ በኋላ መግደላዊት ማርያም የያዕቆብም እናት ማርያም ሰሎሜም መጥተው ሊቀቡት ሽቶ ገዙ።


ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፤ ፈወሳቸውም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios