ማርቆስ 15:45 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከመቶ አለቃውም ተረድቶ በድኑን ለዮሴፍ ሰጠው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሞቱንም ከመቶ አለቃው ካረጋገጠ በኋላ ሥጋውን ለዮሴፍ ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መሞቱንም ከመቶ አለቃው ካረጋገጠ በኋላ ሥጋውን ለዮሴፍ ሰጠው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኢየሱስን መሞት ከመቶ አለቃው ከሰማ በኋላ አስከሬኑን እንዲወስድ ለዮሴፍ ፈቀደለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከመቶ አለቃውም ተረድቶ በድኑን ለዮሴፍ ሰጠው። |
ከዚህም በኋላ አይሁድን ስለፈራ በስውር የጌታችን የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረው የአርማትያስ ሰው ዮሴፍ የጌታችን የኢየሱስን ሥጋ ይወስድ ዘንድ ጲላጦስን ለመነው፤ ጲላጦስም ፈቀደለት። እርሱም ሄዶ የጌታችን የኢየሱስን ሥጋ ወሰደ።