Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዮሐንስ 19:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 ከዚ​ህም በኋላ አይ​ሁ​ድን ስለ​ፈራ በስ​ውር የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ደቀ መዝ​ሙር የነ​በ​ረው የአ​ር​ማ​ት​ያስ ሰው ዮሴፍ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስን ሥጋ ይወ​ስድ ዘንድ ጲላ​ጦ​ስን ለመ​ነው፤ ጲላ​ጦ​ስም ፈቀ​ደ​ለት። እር​ሱም ሄዶ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስን ሥጋ ወሰደ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 ከዚህ በኋላ የአርማትያሱ ዮሴፍ የኢየሱስን በድን ለመውሰድ ጲላጦስን ለመነው፤ ዮሴፍም አይሁድን ስለ ፈራ በስውር የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ነበር። እርሱም ጲላጦስን ካስፈቀደ በኋላ መጥቶ በድኑን ወሰደ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 ከዚህም በኋላ፥ አይሁድን በመፍራት በስውር የኢየሱስ ደቀመዝሙር የነበረው የአርማትያስ ዮሴፍ የኢየሱስን ሥጋ ለመውሰድ ጲላጦስን ለመነ፤ ጲላጦስም ፈቀደለት። ስለዚህም መጥቶ የኢየሱስን ሥጋ ወሰደ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 የአይሁድ ባለሥልጣኖችን በመፍራት በስውር የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረው የአርማትያሱ ዮሴፍ የኢየሱስን አስከሬን ለመውሰድ ጲላጦስን ለመነ። ጲላጦስም ፈቀደለት። ስለዚህ ዮሴፍ ሄዶ አስከሬኑን ወሰደ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 ከዚህም በኋላ አይሁድን ስለ ፈራ በስውር የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረ የአርማትያስ ዮሴፍ የኢየሱስን ሥጋ ሊወስድ ጲላጦስን ለመነ፤ ጲላጦስም ፈቀደለት። ስለዚህም መጥቶ የኢየሱስን ሥጋ ወሰደ።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 19:38
9 Referencias Cruzadas  

ከሕ​ዝቡ አለ​ቆ​ችም ያመ​ኑ​በት ብዙ​ዎች ነበሩ፤ ነገር ግን ከም​ኵ​ራብ አስ​ወ​ጥ​ተው እን​ዳ​ይ​ሰ​ዱ​አ​ቸው በፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ምክ​ን​ያት አል​መ​ሰ​ከ​ሩ​ለ​ትም።


ነገር ግን፥ አይ​ሁ​ድን በመ​ፍ​ራት የእ​ር​ሱን ነገር ገልጦ የተ​ና​ገረ አል​ነ​በ​ረም።


ወላ​ጆቹ አይ​ሁ​ድን ስለ ፈሩ ይህን አሉ፥ “እርሱ ክር​ስ​ቶስ ነው ብሎ በእ​ርሱ የሚ​ያ​ምን ቢኖር ከም​ኵ​ራብ ይውጣ” ብለው አይ​ሁድ ተስ​ማ​ም​ተው ነበ​ርና።


ስለ እር​ሱም የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ ከፈ​ጸሙ በኋላ ከመ​ስ​ቀል አው​ር​ደው በመ​ቃ​ብር ቀበ​ሩት።


ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንም ብዙ​ዎቹ በእ​ስ​ራቴ ምክ​ን​ያት በጌታ ታመኑ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ያለ ፍር​ሀት ጨክ​ነው ያስ​ተ​ምሩ ዘንድ እጅግ ተደ​ፋ​ፈሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos