ማርቆስ 10:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐሥሩም ሰምተው በያዕቆብና በዮሐንስ ይቈጡ ጀመር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐሥሩ ይህን ሲሰሙ፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን መቈጣት ጀመሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዐሥሩ ይህን ሲሰሙ፥ ያዕቆብንና ዮሐንስን መቆጣት ጀመሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቀሩት ዐሥሩ ይህን ሰምተው በያዕቆብና በዮሐንስ ላይ ተቈጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሥሩም ሰምተው በያዕቆብና በዮሐንስ ይቈጡ ጀመር። |
ኢየሱስም ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው “የአሕዛብ አለቆች ተብሎ የምታስቡት እንዲገዙአቸው ታላላቆቻቸውም በላያቸው እንዲሠለጥኑ ታውቃላችሁ።
እርሱም እንዲህ አላቸው፥ “አሕዛብን ንጉሦቻቸው ይገዙአቸዋል፤ በላያቸውም ሥልጣን ያላቸው ቸርነት አድራጊዎች ይባላሉ።
እርስ በርሳችሁ በወንድማማችነት መዋደድ ተዋደዱ፤ የምትራሩም ሁኑ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤ መምህሮቻችሁንም አክብሩ።
በክርክርና ከንቱ ውዳሴን በመውደድ አትሥሩ፤ ትሕትናን በያዘ ልቡና ከራሳችሁ ይልቅ ባልንጀራችሁን አክብሩ እንጂ አትታበዩ።