ማርቆስ 1:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባገኙትም ጊዜ “ሁሉ ይፈልጉሃል፤” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባገኙትም ጊዜ፣ “ሰው ሁሉ ይፈልግሃል!” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባገኙትም ጊዜ፥ “ሰዉ ሁሉ ይፈልግሃል” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባገኙትም ጊዜ፥ “ሰዎች ሁሉ ይፈልጉሃል” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባገኙትም ጊዜ፦ ሁሉ ይፈልጉሃል አሉት። |
ፈሪሳውያንም እርስ በርሳቸው፥ “የምታገኙት ምንም ጥቅም እንደሌለ ታያላችሁን? እነሆ፥ ዓለም ሁሉ ተከትሎታል” ተባባሉ።
ወደ ዮሐንስም ሄደው፥ “መምህር ሆይ፥ በዮርዳኖስ ማዶ ካንተ ጋር የነበረው፥ አንተም የመሰከርህለት እርሱ እነሆ፥ ያጠምቃል፤ ሁሉም ወደ እርሱ ይሄዳል” አሉት።