ማርቆስ 1:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከና አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮሐንስ እስር ቤት ከገባ በኋላ፣ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ወንጌል እየሰበከ ወደ ገሊላ ሄዶ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሐንስ እስር ቤት ከገባ በኋላ፥ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ወንጌል እየሰበከ ወደ ገሊላ መጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሐንስም ተይዞ ወደ እስር ቤት ከገባ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ወንጌል እየሰበከ ወደ ገሊላ መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከና፦ ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ። |
ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ፥ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ፥ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ፥ በከተማዎችና በመንደሮች ሁሉ ይዞር ነበር።
ከዚህም በኋላ ጌታችን ኢየሱስ በየከተማዉና በየመንደሩ ተመላለሰ፤ የእግዚአብሔርንም መንግሥት ሰበከላቸው፤ አስተማራቸውም፤ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርትም ከእርሱ ጋር ነበሩ።
አሁንም እነሆ፥ የእግዚአብሔርን መንግሥት የሰበክሁላችሁ እናንተ ሁላችሁ ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን እንደማታዩኝ እኔ ዐውቄአለሁ።
ከዚህም በኋላ ወደ እርሱ የሚመጡበትን ቀን ቀጠሩትና ብዙዎች ወዳረፈበት ወደ እርሱ መጡ፤ ከጥዋትም ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት እየመሰከረ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስም ከሙሴ ኦሪትና ከነቢያት እየጠቀሰ ነገራቸው።
የእግዚአብሔርን ወንጌል ለማስተማር ተለይቶ ከተጠራ ሐዋርያ፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ከሚሆን ከጳውሎስ፥