ሚልክያስ 1:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሚልክያስ እጅ ለእስራኤል የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ሸክም ይህ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሚልክያስ በኩል ወደ እስራኤል የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ንግር ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሚልክያስ እጅ ለእስራኤል የሆነ የጌታ ቃል ይህ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በነቢዩ በሚልክያስ አማካይነት ለእስራኤል ሕዝብ የተናገረው የትንቢት ቃል ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሚልክያስ እጅ ለእስራኤል የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ሸክም ይህ ነው። |
ይህ ሕዝብ ወይም ነቢይ ወይም ካህን፥ “የእግዚአብሔር ሸክም ምንድር ነው?” ብሎ ቢጠይቅህ፥ አንተ፥ “ሸክሙ እናንተ ናችሁ፤ እጥላችሁማለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር” ትላቸዋለህ።
በንጉሡ በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል በነቢዩ በሐጌ እጅ ወደ ይሁዳ አለቃ ወደ ሰላትያል ልጅ ወደ ዘሩባቤል፥ ወደ ታላቁም ካህን ወደ ኢዮሴዴቅ ልጅ ወደ ኢያሱ እንዲህ ሲል መጣ፦
ስለ እስራኤል የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል ሸክም ይህ ነው። ሰማያትን የዘረጋ፥ ምድርንም የመሠረተ፥ የሰውንም መንፈስ በውስጡ የሠራ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
የእግዚአብሔር ቃል ሸክም በሴድራክ ምድር ላይ ነው፥ በደማስቆም ላይ ያርፋል፣ የእግዚአብሔር ዓይን ወደ ሰውና ወደ እስራኤል ነገድ ሁሉ ዘንድ ነው፣
እግዚአብሔር የወደደውን መቅደስ ይሁዳ አርክሶአልና፥ የእንግዳውንም አምላክ ልጅ ሚስት አድርጎ አግብቶአልና ይሁዳ አታልሎአል፥ በእስራኤልና በኢየሩሳሌም ውስጥ ርኵሰት ተሠርቶአል።