La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 9:60 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ሙታ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ይቀ​ብሩ ዘንድ ሙታ​ንን ተዉ​አ​ቸው፤ አንተ ግን ሂድና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት ስበክ” አለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኢየሱስም፣ “ሙታን ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ተዋቸው፤ አንተ ግን ሄደህ የእግዚአብሔርን መንግሥት ስበክ” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢየሱስም፦ “ሙታኖቻቸውን እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው፤ አንተስ ሄደህ የእግዚአብሔርን መንግሥት አስተምር፤” አለው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢየሱስም “ሙታንን ተዋቸው፤ ሙታኖቻቸውን ይቅበሩ፤ አንተ ግን ሂድና ስለ እግዚአብሔር መንግሥት አስተምር!” ሲል መለሰለት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢየሱስም፦ ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው፤ አንተስ ሄደህ የእግዚአብሔርን መንግሥት ስበክ አለው።

Ver Capítulo



ሉቃስ 9:60
14 Referencias Cruzadas  

ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዞር ነበር።


ኢየሱስ “ተከተለኝ፤ ሙታናቸውንም እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው፤” አለው።


ይህ ልጄ ሞቶ ነበር፤ አሁን ግን ሕያው ሆኖ​አ​ልና፥ ጠፍ​ቶም ነበር፤ ተገ​ኝ​ቶ​አ​ልና ደስ ይላ​ቸ​ውም ጀመር።


ነገር ግን ይህ ወን​ድ​ምህ ሞቶ ነበረ፤ ሕያው ሆኖ​አ​ልና፥ ጠፍ​ቶም ተገ​ኝ​ቶ​አ​ልና፥ ደስ ሊለን፥ ሐሤ​ትም ልና​ደ​ርግ ይገ​ባል።”


ወን​ጌ​ልን ባስ​ተ​ም​ርም መመ​ስ​ገን አይ​ገ​ባ​ኝም፤ ታዝዤ አድ​ር​ጌ​ዋ​ለ​ሁና፤ ወን​ጌ​ልን ባላ​ስ​ተ​ምር ደግሞ ወዮ​ልኝ።


እና​ን​ተም በኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ ምው​ታን ሆና​ችሁ ነበር።


በኃ​ጢ​አ​ታ​ችን የሞ​ትን ሳለን በክ​ር​ስ​ቶስ ሕይ​ወ​ትን ሰጠን፤ በጸ​ጋ​ውም ዳንን።


ቅምጥሊቱ ግን በሕይወትዋ ሳለች የሞተች ናት።


ቃሉን ስበክ፤ በጊዜውም አለጊዜውም ጽና፤ ፈጽመህ እየታገሥህና እያስተማርህ ዝለፍና ገሥጽ፤ ምከርም።


አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ፤ መከራን ተቀበል፤ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አድርግ፤ አገልግሎትህን ፈጽም።


“በሰርዴስም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስትና ሰባቱ ከዋክብት ያሉት እንዲህ ይላል “ሥራህን አውቃለሁ፤ ሕያው እንደ መሆንህ ስም አለህ፤ ሞተህማል።