ከግብፅ ሀገር አወጣቸው ዘንድ እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ያለ ቃል ኪዳን አይደለም፤ እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና፥ እኔም ቸል አልኋቸው፥ ይላል እግዚአብሔር።
ሉቃስ 8:54 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ግን ሁሉን ወደ ውጭ አስወጣና እጅዋን ይዞ ጠራት፤ እንዲህም አላት፥ “ አንቺ ብላቴና ተነሺ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ግን እጇን ይዞ፣ “ልጄ ሆይ፤ ተነሺ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ግን እጅዋን ይዞ፦ “አንቺ ልጅ! ተነሺ፤” ብሎ ተጣራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ የልጅትዋን እጅ ይዞ፦ “አንቺ ልጅ፥ ተነሽ!” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ግን እጅዋን ይዞ፦ አንቺ ብላቴና፥ ተነሺ ብሎ ጮኸ። |
ከግብፅ ሀገር አወጣቸው ዘንድ እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ያለ ቃል ኪዳን አይደለም፤ እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና፥ እኔም ቸል አልኋቸው፥ ይላል እግዚአብሔር።
ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ከጴጥሮስ፥ ከያዕቆብና ከዮሐንስ፥ ከብላቴናይቱም አባትና እናት በቀር ማንም ከእርሱ ጋር ሌላ ሰው ይገባ ዘንድ አልፈቀደም።
አብ ሙታንን እንደሚያስነሣቸው፥ ሕይወትንም እንደሚሰጣቸው እንዲሁ ወልድም ለሚወድዳቸው ሕይወትን ይሰጣል።
ጴጥሮስም ሁሉን ካስወጣ በኋላ ተንበርክኮ ጸለየ፤ ወደ በድንዋም መለስ ብሎ፥ “ጣቢታ ሆይ፥ ተነሽ” አላት፤ እርስዋም ዐይኖችዋን ገለጠች፤ ያንጊዜም ጴጥሮስን አየችው፤ ቀና ብላም ተቀመጠች።
“ለብዙዎች አሕዛብ አባት አደርግሃለሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈ ሙታንን በሚያስነሣቸው፥ የሌሉትንም እንደ አሉ በሚያደርጋቸው በአመነበት በእግዚአብሔር ፊት አብርሃም የሁላችን አባት ነው።