ሉቃስ 8:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዕድሜዋ ዐሥራ ሁለት ዓመት የሚሆናት አንዲት ልጅ ነበረችው፤ እርስዋም ልትሞት ቀርባ ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ልመና ያቀረበው ዕድሜዋ ዐሥራ ሁለት ዓመት የሆነ አንዲት ልጅ ስለ ነበረችው ነው፤ እርሷ በሞት አፋፍ ላይ ነበረች። ወደዚያው እያመራ ሳለ፣ ሕዝቡ በመጋፋት እጅግ ያጨናንቀው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዐሥራ ሁለት ዓመት የሚሆናት አንዲት ሴት ልጅ ነበረችውና፤ እርሷም ለመሞት እያጣጣረች ነበር። ሲሄድም ሕዝቡ በዙርያው እየተጋፉት ያጨናንቁት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ያለው ዕድሜዋ ዐሥራ ሁለት ዓመት የሆናት አንድያ ልጁ ታማ በሞት አፋፍ ላይ ስለ ነበረች ነው። ኢየሱስም ከእርሱ ጋር አብሮ ሲሄድ ሳለ ተከትለውት የነበሩ ብዙ ሰዎች በመጨናነቅ ይጋፉ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሥራ ሁለት ዓመት የሆናት አንዲት ሴት ልጅ ነበረችውና፤ እርስዋም ለሞት ቀርባ ነበረች። ሲሄድም ሕዝቡ ያጨናንቁት ነበር። |
ሰው በከንቱ ወራቱ ቍጥርና እንደ ጥላ በሚያሳልፈው ዘመኑ በሕይወቱ ሳለ ለሰው የሚሻለውን የሚያውቅ ማን ነው? ወይስ ለሰው ከፀሓይ በታች ከእርሱ በኋላ የሚሆነውን ማን ይነግረዋል?
“የሰው ልጅ ሆይ! እነሆ የዐይንህን አምሮት በመቅሠፍት እወስድብሃለሁ፤ አንተም ዋይ አትበል፤ አታልቅስም፤ እንባህንም አታፍስስ።
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ! ኀይላቸውን፥ የተመኩበትንም ደስታ፥ የዐይናቸውንም አምሮት፥ የነፍሳቸውንም ምኞት፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በወሰድሁባቸው ቀን፥
በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፣ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፣ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።
ወደ ከተማው በር በደረሰ ጊዜም እነሆ፥ ያንዲት መበለት ሴት ልጅ ሙቶ ሬሳውን ተሸክመው ሲሄዱ አገኘ፤ ይኸውም ለእናቱ አንድ ነበረ፤ ብዙዎችም የከተማ ሰዎች አብረዋት ነበሩ።
እነሆም ኢያኢሮስ የሚባል ሰው መጣ፤ እርሱም የምኵራብ ሹም ነበር፤ ከጌታችን ኢየሱስ እግር በታችም ሰገደ። ወደ ቤቱም ይገባ ዘንድ ለመነው።
ከዚህም በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ከእርሱ ጋር ሲሄድ ሰዎች ያጨናንቁት ነበር፤ ከዐሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም ይፈስሳት የነበረች ሴት መጣች፤ ገንዘብዋንም ሁሉ ለባለመድኀኒቶች ሰጥታ ጨርሳ ነበር፤ ነገር ግን ሊያድናት የቻለ ማንም አልነበረም።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “ማን ዳሰሰኝ?” አለ፤ ሁሉም ካዱ፤ ጴጥሮስና ከእርሱ ጋር የነበሩትም፥ “መምህር ሆይ፥ ሰው ይጋፋህና ያጨናንቅህ የለምን? አንተ ግን ማን ዳሰሰኝ? ትላለህ” አሉት።
ስለዚህም በአንድ ሰው በደል ምክንያት ኀጢአት ወደ ዓለም ገባች፤ ስለዚችም ኀጢአት ሞት ገባ፤ እንደዚሁም ሁሉ ኀጢአትን ስለ አደረጉ በሰው ሁሉ ላይ ሞት መጣ።