La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 6:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም፥ “በሰ​ን​በት ሊደ​ረግ የማ​ይ​ገ​ባ​ውን ለምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ?” አሉ​አ​ቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከፈሪሳውያን መካከል አንዳንዶቹ ግን፣ “በሰንበት ቀን ያልተፈቀደውን ለምን ታደርጋላችሁ?” አሏቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከፈሪሳውያን ወገን የሆኑ አንዳንዶች ግን እንዲህ አሉ፦ “በሰንበት ቀን ያልተፈቀደውን ስለምን ታደርጋላችሁ?”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ ደቀ መዛሙርቱን “በሰንበት ቀን ሊደረግ የማይገባውን ነገር ስለምን ታደርጋላችሁ?” አሉአቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከፈሪሳውያን ግን አንዳንዶቹ፦ በሰንበት ሊያደርግ ያልተፈቀደውን ስለ ምን ታደርጋላችሁ? አሉአቸው።

Ver Capítulo



ሉቃስ 6:2
14 Referencias Cruzadas  

“ሰው በባ​ል​ን​ጀ​ራው ዘንድ አህያ ወይም በሬ ወይም በግ ወይም ሌላ እን​ስሳ እን​ዲ​ጠ​ብ​ቅ​ለት አደራ ቢያ​ኖር፥ ማንም ሳያይ ቢሞት ወይም ቢጐዳ ወይም ቢማ​ረክ፥


ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ሥራ፤ ሰባ​ተ​ኛዋ ቀን ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደ​ስች የዕ​ረ​ፍት ሰን​በት ናት፤ በሰ​ን​በት ቀን የሚ​ሠራ ሁሉ ፈጽሞ ይገ​ደል።


ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ትሠ​ራ​ለህ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ታር​ፋ​ለህ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ የዕ​ረ​ፍት ሰን​በት ነው፤ የሚ​ሠ​ራ​በ​ትም ሁሉ ይሙት።


ፈቃ​ድ​ህን በተ​ቀ​ደ​ሰው ቀኔ ከማ​ድ​ረግ እግ​ር​ህን ከሰ​ን​በት ብት​መ​ልስ፥ ሰን​በ​ት​ንም ደስታ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ቀ​ደሰ ብታ​ደ​ር​ገው፥ ክፉ ሥራን ለመ​ሥ​ራት እግ​ር​ህን ባታ​ነሣ፥ በአ​ፍ​ህም ክፉ ነገ​ርን ባት​ና​ገር፥


ፈሪሳውያንም አይተው “እነሆ ደቀ መዛሙርትህ በሰንበት ማድረግ ያልተፈቀደውን ያደርጋሉ፤” አሉት።


“ደቀ መዛሙርትህ ስለ ምን የሽማግሎችን ወግ ይተላለፋሉ? እንጀራ ሲበሉ እጃቸውን አይታጠቡምና፤” አሉት።


ፈሪሳውያንም “እነሆ፥ በሰንበት ያልተፈቀደውን ስለ ምን ያደርጋሉ?” አሉት።


እነ​ር​ሱም፥ “የዮ​ሐ​ንስ ደቀ መዛ​ሙ​ርት ስለ​ምን በብዙ ይጾ​ማሉ? ጸሎ​ትስ ስለ​ምን ያደ​ር​ጋሉ? የፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ወገ​ኖች የሆ​ኑ​ትም ስለ​ምን እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋሉ? ያንተ ደቀ መዛ​ሙ​ርት ግን ለምን ይበ​ላሉ? ይጠ​ጣ​ሉም?” አሉት።


ስለ​ዚ​ህም አይ​ሁድ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ያሳ​ድ​ዱ​ትና ሊገ​ድ​ሉ​ትም ይሹ ነበር፤ በሰ​ን​በት እን​ዲህ ያደ​ርግ ነበ​ርና።