ሉቃስ 3:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቃይናን ልጅ፥ የአርፋክስድ ልጅ፥ የሴም ልጅ፥ የኖኅ ልጅ፥ የላሜሕ ልጅ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቃይንም ልጅ፣ የአርፋክስድ ልጅ፣ የሴም ልጅ፣ የኖኅ ልጅ፣ የላሜህ ልጅ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቃይናን ልጅ፥ የአርፋክስድ ልጅ፥ የሴም ልጅ፥ የኖኅ ልጅ፥ የላሜህ ልጅ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሼላሕ የቃይንም ልጅ፥ ቃይንም የአርፋክስድ ልጅ፥ አርፋክስድ የሴም ልጅ፥ ሴም የኖኅ ልጅ፥ ኖኅ የላሜሕ ልጅ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቃይንም ልጅ፥ የአርፋክስድ ልጅ፥ የሴም ልጅ፥ የኖኅ ልጅ፥ የላሜህ ልጅ፥ |
በዚያውም ቀን ኖኅ ወደ መርከብ ገባ፤ የኖኅ ልጆችም ሴም፥ ካም፥ ያፌትና የኖኅ ሚስት፥ ሦስቱም የልጆቹ ሚስቶች ከእርሱ ጋር ገቡ።
በምድር ላይ የነበረውም ሁሉ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ፥ እስከሚርመሰመሰውም ሁሉ ድረስ፥ እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ ተደመሰሰ፤ ከምድርም ተደመሰሱ። ኖኅም አብረውት በመርከብ ከነበሩት ጋር ብቻውን ቀረ።
እግዚአብሔርም ኖኅን፥ በመርከብም ከእርሱ ጋር የነበረውን አራዊቱን ሁሉ፥ እንስሳውንም ሁሉ፥ አዕዋፍንም ሁሉ፥ የሚንቀሳቀሰውንም ሁሉ ዐሰበ፤ እግዚአብሔርም በምድር ላይ ነፋስን አመጣ፤ ውኃውም ጐደለ፤
እነዚህ ሦስቱ ሰዎች ኖኅና ዳንኤል ኢዮብም በመካከልዋ ቢኖሩ በጽድቃቸው የገዛ ነፍሳቸውን ያድናሉ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ኖኅ ወደ መርከብ እስከ ገባበት ቀን ድረስ ሲበሉና ሲጠጡ፥ ሲያገቡና ሲጋቡ ነበረ፤ የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን አንድ አድርጎ አጠፋ።
ኖኅም ስለማይታየው ነገር የነገሩትን ባመነ ጊዜ ፈራ፤ ቤተ ሰቡንም ያድን ዘንድ ክፍል ያላት መርከብን ሠራ፤ በዚህም ዓለምን አስፈረደበት፤ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።