Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 3:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ሼላሕ የቃይንም ልጅ፥ ቃይንም የአርፋክስድ ልጅ፥ አርፋክስድ የሴም ልጅ፥ ሴም የኖኅ ልጅ፥ ኖኅ የላሜሕ ልጅ፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 የቃይንም ልጅ፣ የአርፋክስድ ልጅ፣ የሴም ልጅ፣ የኖኅ ልጅ፣ የላሜህ ልጅ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 የቃይናን ልጅ፥ የአርፋክስድ ልጅ፥ የሴም ልጅ፥ የኖኅ ልጅ፥ የላሜህ ልጅ፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 የቃ​ይ​ናን ልጅ፥ የአ​ር​ፋ​ክ​ስድ ልጅ፥ የሴም ልጅ፥ የኖኅ ልጅ፥ የላ​ሜሕ ልጅ፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 የቃይንም ልጅ፥ የአርፋክስድ ልጅ፥ የሴም ልጅ፥ የኖኅ ልጅ፥ የላሜህ ልጅ፥

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 3:36
22 Referencias Cruzadas  

እንዲሁም የጽድቅ ሰባኪ የነበረውን ኖኅን ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋር አድኖ እግዚአብሔርን የማያመልኩ ሰዎች በነበሩበት ዓለም ላይ የጥፋትን ውሃ ሲያመጣ ራርቶ የቀድሞውን ዓለም አልማረውም፤


እነዚህ በወህኒ ቤት የነበሩ መናፍስት ቀድሞ በኖኅ ዘመን መርከብ ሲዘጋጅ እግዚአብሔር በትዕግሥት ሲጠብቃቸው ሳለ አንታዘዝም ያሉ ናቸው። በዚያ መርከብ ውስጥ ገብተው በውሃ አማካይነት የዳኑት ቊጥራቸው ስምንት የሆነ ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው።


ገና በዐይን ስለማይታዩት ነገሮች እግዚአብሔር ባስጠነቀቀው ጊዜ ኖኅ እግዚአብሔርን በመፍራት ቤተሰቡን ለማዳን መርከብን የሠራው በእምነት ነው፤ በኖኅም እምነት ዓለም ኃጢአተኛ መሆኑ ታውቆ ተፈረደበት፤ ኖኅም በእምነት የሚገኘውን ጽድቅ ወረሰ።


ኖኅ ወደ መርከብ እስከ ገባበት ቀን ድረስ ሰዎች ሲበሉና ሲጠጡ፥ ሲያገቡና ሲጋቡም ነበር፤ በዚያን ጊዜ የጥፋት ውሃ መጣና አጥለቅልቆ ሁሉንም አጠፋቸው።


እነዚያ ሦስት ሰዎች ማለትም ኖኅ፥ ዳንኤልና ኢዮብ በውስጥዋ ቢገኙ እንኳ በደግነታቸው ማትረፍ የሚችሉት የራሳቸውን ሕይወት ብቻ ነው፤ ይህን የተናገረ ጌታ እግዚአብሔር ነው።


የሴም ልጆች፦ ዔላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ፥ አራም፥ ዑፅ፥ ሑል፥ ጌቴርና ሜሼክ ሲሆኑ፥ እነርሱም በስሞቻቸው ለሚጠሩ ሕዝቦች የነገድ አባቶች ናቸው።


ከመርከቡ የወጡት የኖኅ ልጆች ሴም፥ ካምና ያፌት ናቸው፤ ካም የከነዓን አባት ነው፤


እግዚአብሔር ኖኅንና ልጆቹን ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፤ “ብዙ፥ ተባዙ ምድርንም ሙሉአት፤


እግዚአብሔር ኖኅንና ከእርሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩትን አራዊትና እንስሶች ሁሉ አሰበ፤ ነፋስ በምድር ላይ እንዲነፍስ አደረገ፤ ውሃውም መጒደል ጀመረ።


እግዚአብሔር በምድር ላይ ያለውን ሕያው ፍጥረት ሁሉ፥ ሰዎችንም፥ እንስሶችንም፥ ወፎችንም፥ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶች ሳይቀሩ ሁሉንም አጠፋ። ከሞት የተረፉት ኖኅና ከእርሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩት ብቻ ነበሩ።


ዝናቡ መዝነብ በጀመረበት ቀን፥ ኖኅና ሚስቱ ከልጆቻቸው ከሴም፥ ከካም፥ ከያፌትና ከሦስቱም ልጆቻቸው ሚስቶች ጋር ወደ መርከቡ ገቡ።


ኖኅም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ አደረገ።


አዳም መቶ ሠላሳ ዓመት በሆነው ጊዜ በመልኩና በአምሳያው እርሱን የሚመስል ወንድ ልጅ ወለደ፤ “ሤት” የሚል ስምም አወጣለት።


አዳም ሤትን ወለደ፤ ሤት ሄኖስን ወለደ፤ ሄኖስ ቃይናንን ወለደ፤


ናኮር የሰሩግ ልጅ፥ ሰሩግ የረዑ ልጅ፥ ረዑ የፌሌግ ልጅ፥ ፋሌቅ የዔቤር ልጅ፥ ዔቤር የሼላሕ ልጅ፥


ላሜሕ የማቱሳላ ልጅ፥ ማቱሳላ የሔኖክ ልጅ፥ ሔኖክ የያሬድ ልጅ፥ ያሬድ የመላልኤል ልጅ፥ መላልኤል የቃይናን ልጅ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios