እስራኤልም ሁሉ ንጉሡ እንዳልሰማቸው ባዩ ጊዜ ሕዝቡ ለንጉሡ፥ “በዳዊት ዘንድ ምን ክፍል አለን? በእሴይም ልጅ ዘንድ ርስት የለንም። እስራኤል ሆይ፥ ወደ ድንኳኖቻችሁ ተመለሱ፤ ዳዊት ሆይ፥ አሁን የራስህን ቤት ተመልከት” ብለው መለሱለት። እስራኤልም ወደየቤታቸው ተመለሱ።
ሉቃስ 3:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዕሤይ ልጅ፥ የኢዮቤድ ልጅ፥ የቦዔዝ ልጅ፥ የሰልሞን ልጅ፥ የነዓሶን ልጅ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእሴይ ልጅ፣ የኢዮቤድ ልጅ፣ የቦዔዝ ልጅ፣ የሰልሞን ልጅ፣ የነአሶን ልጅ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእሴይ ልጅ፥ የኢዮቤድ ልጅ፥ የቦዔዝ ልጅ፥ የሰልሞን ልጅ፥ የነአሶን ልጅ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት የእሴይ ልጅ፥ እሴይ የኢዮቤድ ልጅ፥ ኢዮቤድ የቦዔዝ ልጅ፥ ቦዔዝ የሰልሞን ልጅ፥ ሰልሞን የነአሶን ልጅ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዳዊት ልጅ፥ የእሴይ ልጅ፥ የኢዮቤድ ልጅ፥ የቦዔዝ ልጅ፥ የሰልሞን ልጅ፥ |
እስራኤልም ሁሉ ንጉሡ እንዳልሰማቸው ባዩ ጊዜ ሕዝቡ ለንጉሡ፥ “በዳዊት ዘንድ ምን ክፍል አለን? በእሴይም ልጅ ዘንድ ርስት የለንም። እስራኤል ሆይ፥ ወደ ድንኳኖቻችሁ ተመለሱ፤ ዳዊት ሆይ፥ አሁን የራስህን ቤት ተመልከት” ብለው መለሱለት። እስራኤልም ወደየቤታቸው ተመለሱ።
በመጀመሪያ በምሥራቅ በኩል የሚሰፍሩት ከሠራዊቶቻቸው ጋር የይሁዳ ሰፈር ሰዎች ይሆናሉ፤ የይሁዳ ልጆችም አለቃ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበረ።
ለደኅንነትም መሥዋዕት ሁለት ጊደሮች፥ አምስት አውራ በጎች፥ አምስት አውራ ፍየሎች፥ አምስት የአንድ ዓመት እንስት የበግ ጠቦቶች ነበረ፤ የአሚናዳብ ልጅ የነአሶን መባ ይህ ነበረ።
የእሴይ ልጅ በምድር ላይ በሕይወት በሚኖርበት ዘመን ሁሉ መንግሥትህ አትጸናም፤ አሁንም ሞት የሚገባው ነውና ያን ብላቴና ያመጡት ዘንድ ላክ” አለው።