አላቸውም፥ “ጌቶች ሆይ፥ ወደ ባሪያችሁ ቤት ገብታችሁ እደሩ፤ እግራችሁንም ታጠቡ፤ ነገም ማልዳችሁ መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ።” እነርሱም፥ “በአደባባዩ እናድራለን እንጂ፥ አይሆንም” አሉት።
ሉቃስ 24:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሊሄዱባት ወደ ነበረችው መንደርም ተቃረቡ፤ እርሱ ግን ይርቃቸው ጀመር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደሚሄዱበትም መንደር በተቃረቡ ጊዜ፣ ኢየሱስ ዐልፎ የሚሄድ መሰለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደሚሄዱበትም መንደር ቀረቡ፤ እርሱም አልፎ የሚሄድ መሰለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ወደሚሄዱበት መንደር በቀረቡ ጊዜ ኢየሱስ አልፎ የሚሄድ መሰለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደሚሄዱበትም መንደር ቀረቡ፥ እርሱም ሩቅ የሚሄድ መሰላቸው። |
አላቸውም፥ “ጌቶች ሆይ፥ ወደ ባሪያችሁ ቤት ገብታችሁ እደሩ፤ እግራችሁንም ታጠቡ፤ ነገም ማልዳችሁ መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ።” እነርሱም፥ “በአደባባዩ እናድራለን እንጂ፥ አይሆንም” አሉት።
ዮሴፍም ወንድሞቹን በአያቸው ጊዜ ዐወቃቸው፤ እንደማያውቃቸውም ሆነ፤ ክፉ ቃልንም ተናገራቸው፥ “እናንተ ከወዴት መጣችሁ?” አላቸው። እነርሱም፥ “ከከነዓን ምድር እህል ልንሸምት የመጣን ነን” አሉት።
ነፋስ ከወደ ፊታቸው ነበረና እየቀዘፉ ሲጨነቁ አይቶ፥ ከሌሊቱ በአራተኛው ክፍል በባሕር ላይ እየሄደ ወደ እነርሱ መጣ፤ ሊያልፋቸውም ይወድ ነበር።
እነርሱም፥ “መሽቶአልና፥ ፀሐይም ተዘቅዝቆአልና፥ ከእኛ ጋር እደር” ብለው ግድ አሉት፤ ከእነርሱም ጋር ሊያድር ገባ።