Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 24:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 እነ​ር​ሱም፥ “መሽ​ቶ​አ​ልና፥ ፀሐ​ይም ተዘ​ቅ​ዝ​ቆ​አ​ልና፥ ከእኛ ጋር እደር” ብለው ግድ አሉት፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሊያ​ድር ገባ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 እነርሱ ግን፣ “ምሽት እየተቃረበ፣ ቀኑም እየተገባደደ ስለ ሆነ ከእኛ ጋራ ዕደር” ብለው አጥብቀው ለመኑት፤ ስለዚህ ከእነርሱ ጋራ ለማደር ገባ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 እነርሱ ግን “እኛ ጋር እደር፤ እየመሸ ነው፥ ቀኑም እያለቀ ነውና፤” ሲሉ አጥብቀው ለመኑት፤ እርሱም እነርሱ ጋር ሊያድር ገባ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 እነርሱ ግን “ቀኑ መሽቶአል፤ ፀሐይም መጥለቅዋ ነው፤ ስለዚህ ከእኛ ጋር እዚህ ዕደር” ብለው አጥብቀው ለመኑት፤ በዚህ ምክንያት ከእነርሱ ጋር ሊያድር ወደ ቤት ገባ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 እነርሱ፦ ከእኛ ጋር እደር፥ ማታ ቀርቦአልና ቀኑም ሊመሽ ጀምሮአል ብለው ግድ አሉት፤ ከእነርሱም ጋር ሊያድር ገባ።

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 24:29
6 Referencias Cruzadas  

ከዚ​ህም በኋላ አንድ ቀን እን​ዲህ ሆነ፤ ኤል​ሳዕ ወደ ሱማን አለፈ፤ በዚ​ያም ታላቅ ሴት ነበ​ረች፤ እን​ጀ​ራም ይበላ ዘንድ አቆ​መ​ችው፤ በዚ​ያም ባለፈ ቍጥር እን​ጀራ ሊበላ ወደ​ዚያ ይገባ ነበር።


እር​ሱም ግድ አላ​ቸው፤ ወደ እር​ሱም አቀኑ፤ ወደ ቤቱም ገቡ፤ ቂጣ​ንም አስ​ጋ​ገ​ረ​ላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም በሉ።


ጌታ​ውም አገ​ል​ጋ​ዩን፦ ወደ መን​ገ​ዶ​ችና ወደ ከተ​ማው ቅጥር ፈጥ​ነህ ሂድና ቤቴ እን​ዲ​መላ ይገቡ ዘንድ ግድ በላ​ቸው አለው።


በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ቀይ ሐር የም​ት​ሸጥ ከት​ያ​ጥ​ሮን ሀገር የመ​ጣች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ፈራ አን​ዲት ሴት ነበ​ረች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ልቡ​ና​ዋን ከፍ​ቶ​ላት ነበ​ርና ጳው​ሎስ የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ረ​ውን ታዳ​ምጥ ነበር፤ ስም​ዋም ልድያ ይባል ነበር።


ሊሄ​ዱ​ባት ወደ ነበ​ረ​ችው መን​ደ​ርም ተቃ​ረቡ፤ እርሱ ግን ይር​ቃ​ቸው ጀመር።


ከዚ​ህም በኋላ አብ​ሮ​አ​ቸው ለማ​ዕድ ተቀ​ምጦ ሳለ እን​ጀ​ራ​ውን አን​ሥቶ ባረከ፤ ቈር​ሶም ሰጣ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios