ሉቃስ 21:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዓለም ላይ ከሚመጣው ፍርሀትና ሽብር የተነሣም የሰዎች ነፍስ ትዝላለች፤ ያንጊዜ የሰማያት ኀይል ይናወጣልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰማያት ኀይላት ስለሚናወጡ፣ ሰዎች በፍርሀትና በዓለም ላይ ምን ይመጣ ይሆን እያሉ በመጠባበቅ ይዝላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰማያት ኀይላት ይናወጣሉና፥ ሰዎችም ከፍርሃትና በዓለም ላይ የሚመጣውን ከመጠበቅ የተነሣ ይደክማሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዓለም ላይ የሚመጣውን ነገር በመጠባበቅ ሰዎች በፍርሃት ይሸበራሉ፤ በዚያን ጊዜ የሰማይ ኀይሎች ይናወጣሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰዎችም ከፍርሃትና በዓለም የሚመጣበትን ከመጠበቅ የተነሣ ይደክማሉ፤ የሰማያት ኃይላት ይናወጣሉና። |
በጠላቶቻቸውም ምድሮች ሳሉ ከእናንተ ተለይተው በቀሩት ላይ በልባቸው ድንጋጤን እሰድድባቸዋለሁ፤ በነፋስም የምትንቀሳቀስ የቅጠል ድምፅ ታሸብራቸዋለች፤ ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሸሻሉ ፤
“በፀሐይና በጨረቃ፥ በከዋክብትም ላይ ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አሕዛብ ይጨነቃሉ፤ ከባሕሩና ከሞገዱ ድምፅ የተነሣም ይሸበራሉ።