እነሆ፥ እኔና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች ለእስራኤል በጽዮን ተራራ ከሚኖረው ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምልክትና ተአምራት ነን።
ሉቃስ 2:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍና እናቱ ግን በእርሱ ላይ ስለሚናገረው ያደንቁ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባቱና እናቱም ስለ እርሱ በተነገረው ነገር ተገረሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍና እናቱም ስለ እርሱ በተባሉት ነገሮች ይደነቁ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሴፍና ማርያም ስለ ሕፃኑ በተባለው ነገር ሁሉ ይደነቁ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍና እናቱም ስለ እርሱ በተባለው ነገር ይደነቁ ነበር። |
እነሆ፥ እኔና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች ለእስራኤል በጽዮን ተራራ ከሚኖረው ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምልክትና ተአምራት ነን።
በአዩትም ጊዜ ደነገጡ፤ እናቱም፥ “ልጄ፥ ለምን እንዲህ አደረግኸን? እነሆ አባትህም፥ እኔም ስንፈልግህ ደከምን” አለችው።