ሉቃስ 2:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአሕዛብ ብርሃንን፥ ለወገንህ ለእስራኤልም ክብርን ትገልጥ ዘንድ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ለአሕዛብ መገለጥን የሚሰጥ ብርሃን፣ ለሕዝብህ ለእስራኤልም ክብር ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም ለአሕዛብ ሁሉን የሚገልጥ ብርሃን፥ ለሕዝብህም ለእስራኤል ክብር ነው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ለአሕዛብ እውነትን የሚገልጥ ብርሃን ይሆናል፤ ለሕዝብህም ለእስራኤል ክብር ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህም ለአሕዛብ ሁሉን የሚገልጥ ብርሃን ለሕዝብህም ለእስራኤል ክብር ነው። |
በዚያም ቀን የእሴይ ሥር ይቆማል፤ የተሾመውም የአሕዛብ አለቃ ይሆናል፤ አሕዛብም በእርሱ ተስፋ ያደርጋሉ፤ ማረፊያውም የተከበረ ይሆናል።
በዚያም ቀን እግዚአብሔር ከእስራኤል የተረፉትን ያከብርና ከፍ ያደርግ ዘንድ በጌትነቱ ምክር በምድር ላይ ያበራል።
እርሱም፥ “የያዕቆብን ነገዶች እንደገና እንድታስነሣ፥ ከእስራኤልም የተበተኑትን ወደ አባቶች ቃል ኪዳን እንድትመልስ ባርያዬ ትሆን ዘንድ ለአንተ እጅግ ታላቅ ነገር ነውና፥ እስከ ምድር ዳር ድረስ መድኀኒት ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ” ይላል።
የተጋዙትንም፦ ውጡ፤ በጨለማም የተቀመጡትን፦ ተገለጡ፤ ትል ዘንድ።” በመንገድም ሁሉ ላይ ይሰማራሉ፤ ማሰማሪያቸውም በጥርጊያ ጎዳና ሁሉ ላይ ይሆናል።
ሕዝቤ ሆይ፥ ስሙኝ፤ ስሙኝ፤ እናንተም ነገሥታት ተግሣጼን አድምጡኝ፤ ሕግ ከእኔ ይወጣልና፥ ፍርዴም ለአሕዛብ ብርሃን ይሆናልና።
ፀሐይ በቀን የሚያበራልሽ አይደለም፤ በሌሊትም ጨረቃ የሚወጣልሽ አይደለም፤ ለአንቺስ እግዚአብሔር የዘለዓለም ብርሃንሽ፥ አምላክሽም ክብርሽ ይሆናል።
አሕዛብ አማልክት ያልሆኑ አማልክቶቻቸውን ይለውጡ አንደ ሆነ እዩ፤ ነገር ግን ሕዝቤ ክብራቸውን ለማይረባ ነገር ለወጡ።
መልአኩም እንዲህ አላቸው፥ “እነሆ፥ ለእናንተና ለሕዝቡ ሁሉ ደስታ የሚሆን ታላቅ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ።
ክርስቶስ እንደሚሞት፥ ከሙታን ተለይቶም አስቀድሞ እንደሚነሣ፥ ለሕዝብና ለአሕዛብ ሁሉ፥ ለመላውም ዓለም እንደሚያበራ።”