ሉቃስ 19:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ ያላኖርኸውን የምትወስድ፥ ያልዘራኸውን የምታጭድ፥ ያልበተንኸውንም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንህ ስለማውቅህ ፈርቼሃለሁና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ ያላስቀመጥኸውን የምትወስድ፣ ያልዘራኸውን የምታጭድ ጨካኝ ሰው ስለ ሆንህ ፈራሁህ።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርቼሃለሁና፥ ጨካኝ ሰው ስለ ሆንክ፤ ያላስቀመጥከውን የምትወስድ፤ ያልዘራኸውንም የምታጭድ ነህና፤’ አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ያደረግኹት አንተ ያላስቀመጥከውን የምትወስድ፥ ያልዘራኸውንም የምትሰበስብ፥ ኀይለኛ ሰው መሆንህን ዐውቄ ስለ ፈራሁህ ነው’ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርቼሃለሁና፥ ጨካኝ ሰው ስለ ሆንህ፤ ያላኖርኸውን ትወስዳለህ ያልዘራኸውንም ታጭዳለህ አለው። |
ጌታውም እንዲህ አለው፦ አንተ ክፉ ሰነፍ አገልጋይ፥ እኔ ያላስቀመጥሁትን የምወስድ፥ ያልዘራሁትን የማጭድ፥ ያልበተንሁትንም የምሰበስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንሁ ታውቃለህን? እንደ ቃልህ እፈርድብሃለሁ።
ዳግመናም አባ አባት ብለን የምንጮህበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደ ገና ለፍርሀት የባርነት መንፈስን አልተቀበላችሁምና።
ሕግን ሁሉ የሚጠብቅ፥ ነገር ግን በአንዱ የሚሰናከል ማንም ቢኖር በሁሉ በደለኛ ይሆናል፤ “አታመንዝር” ያለው ደግሞ “አትግደል” ብሎአልና፤
ሳሙኤልም ሕዝቡን ሁሉ አላቸው፥ “አትፍሩ፤ በእውነት ይህን ክፋት ሁሉ አደረጋችሁ፤ ነገር ግን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁ አምልኩት እንጂ እግዚአብሔርን ከመከተል ፈቀቅ አትበሉ።