ሕዝብ እንደሚመጣ ወደ አንተ ይመጣሉ፤ እንደ ሕዝቤም በፊትህ ይቀመጣሉ፤ ቃልህንም ይሰማሉ፤ ነገር ግን አያደርጉትም፤ በአፋቸው ሐሰት ነገር አለና፥ ልባቸውም ጣዖታትን ይከተላልና።
ሉቃስ 18:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ግን ይህን ሰምቶ በጣም አዘነ፤ እርሱ እጅግ ባለጸጋ ነበርና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውየው ግን ይህን ሲሰማ፣ ብዙ ሀብት ስለ ነበረው በጣም ዐዘነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ግን እጅግ ሀብታም ነበርና ይህንን ሰምቶ በጣም አዘነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውየው ግን በጣም ሀብታም ስለ ነበረ፥ ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ግን ይህን ሰምቶ እጅግ ባለ ጠጋ ነበርና ብዙ አዘነ። |
ሕዝብ እንደሚመጣ ወደ አንተ ይመጣሉ፤ እንደ ሕዝቤም በፊትህ ይቀመጣሉ፤ ቃልህንም ይሰማሉ፤ ነገር ግን አያደርጉትም፤ በአፋቸው ሐሰት ነገር አለና፥ ልባቸውም ጣዖታትን ይከተላልና።
ጌታችን ኢየሱስም ይህን ሰምቶ እንዲህ አለው፥ “አንዲት ቀርታሃለች፤ ሂድና ያለህን ሁሉ ሸጠህ ለነዳያን ስጥ፤ በሰማይም መዝገብ ታገኛለህ፤ መጥተህም ተከተለኝ።”
ጌታችን ኢየሱስም እጅግ ሲያዝን አይቶ እንዲህ አለ፥ “ገንዘብ ላላቸው ሰዎች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ጭንቅ ነው!
ዘኬዎስም ቆመና ጌታችንን እንዲህ አለው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ አሁን የገንዘቤን እኩሌታ ለነዳያን እሰጣለሁ፤ የበደልሁትም ቢኖር ስለ አንድ ፋንታ አራት እጥፍ እከፍለዋለሁ።”
“ራሳችሁን ጠብቁ፤ በመብልና በመጠጥ፥ በመቀማጠልና የዓለምን ኑሮ በማሰብ ልባችሁን አታደንድኑ፤ ያቺ ቀንም በድንገት ትደርስባችኋለች።
በእሾህም መካከል የወደቀው ቃሉን ሰምተው የባለጠግነት ዐሳብ፥ የኑሮም መቈርቈር የተድላና የደስታ መጣፈጥም የሚአስጨንቃቸውና ፍሬ የማያፈሩ ናቸው።
ሴሰኛ፥ ወይም ኀጢአተኛ፥ ወይም ቀማኛ፥ ወይም ጣዖትን የሚያመልክ ሁሉ በእግዚአብሔር ልጅ በክርስቶስ መንግሥት ዕድል ፋንታ እንደሌለው ይህን ዕወቁ።
ክርስቶስን አገለግለው ዘንድ፥ ሁሉን የተውሁለት፥ እንደ ጕድፍም ያደረግሁለት የጌታዬን የኢየሱስ ክርስቶስን ኀይልና ገናናነት ስለማውቅ ሁሉን እንደ ኢምንት ቈጠርሁት።
ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም።