La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 15:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“ታላቁ ልጁም በእ​ርሻ ነበ​ርና ተመ​ልሶ ወደ ቤቱ አጠ​ገብ በደ​ረሰ ጊዜ የዘ​ፈ​ኑ​ንና የመ​ሰ​ን​ቆ​ውን ድምፅ ሰማ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“በዚህ ጊዜ ታላቁ ልጅ በዕርሻ ቦታ ነበረ፤ ከዚያም ተመልሶ ወደ ቤት በተቃረበ ጊዜ፣ የሙዚቃና የጭፈራ ድምፅ ሰማ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ታላቁ ልጁ በእርሻ ነበረ፤ መጥቶም ወደ ቤት በቀረበ ጊዜ የሙዚቃና የውዝዋዜ ድምፅ ሰማ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“በዚህ ጊዜ ታላቁ ልጅ ለሥራ ወደ እርሻ ወጥቶ ነበር፤ ተመልሶ ሲመጣ ወደ ቤቱ በተቃረበ ጊዜ የሙዚቃና የጭፈራ ድምፅ ሰማ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ታላቁ ልጁ በእርሻ ነበረ፤ መጥቶም ወደ ቤት በቀረበ ጊዜ የመሰንቆና የዘፈን ድምፅ ሰማ፤

Ver Capítulo



ሉቃስ 15:25
12 Referencias Cruzadas  

ዳዊ​ትም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በገና ይደ​ረ​ድር ነበር፤ ዳዊ​ትም ለዐ​ይን የሚ​ያ​ን​ጸ​ባ​ርቅ የሐር ቀሚስ ለብሶ ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትን ካል​ሠራ፥ ቤትን የሚ​ሠሩ በከ​ንቱ ይደ​ክ​ማሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተ​ማን ካል​ጠ​በቀ፥ የሚ​ጠ​ብቁ በከ​ንቱ ይተ​ጋሉ።


ስሙን በደ​ስታ ያመ​ሰ​ግ​ናሉ፥ በከ​በ​ሮና በበ​ገና ይዘ​ም​ሩ​ለ​ታል።


በከ​በ​ሮና በሽ​ብ​ሸባ አመ​ስ​ግ​ኑት፤ አው​ታር በአ​ለው መሣ​ሪ​ያና በእ​ን​ዚራ አመ​ስ​ግ​ኑት።


በጠ​ላ​ቶቼ ሁሉ ዘንድ ተሰ​ደ​ብሁ፥ ይል​ቁ​ንም በጎ​ረ​ቤ​ቶቼ ዘንድ፥ ለዘ​መ​ዶ​ቼም አስ​ፈሪ ሆንሁ፤ በሜዳ ያዩ​ኝም ከእኔ ሸሹ።


የአ​ሮን እኅት ነቢ​ይቱ ማር​ያ​ምም ከበሮ በእ​ጅዋ ወሰ​ደች፤ ሴቶ​ችም ሁሉ በከ​በ​ሮና በዝ​ማሬ በኋ​ላዋ ወጡ።


ለማ​ል​ቀስ ጊዜ አለው፥ ለመ​ሣ​ቅም ጊዜ አለው፤ ዋይ ለማ​ለት ጊዜ አለው፥ ለመ​ዝ​ፈ​ንም ጊዜ አለው።


የእ​ስ​ራ​ኤል ድን​ግል ሆይ እንደ ገና እሠ​ራ​ሻ​ለሁ፤ አን​ቺም ትሠ​ሪ​ያ​ለሽ፤ እንደ ገናም ከበ​ሮ​ሽን አን​ሥ​ተሽ ከዘ​ፋ​ኞች ጋር ትወ​ጫ​ለሽ።


ይህ ልጄ ሞቶ ነበር፤ አሁን ግን ሕያው ሆኖ​አ​ልና፥ ጠፍ​ቶም ነበር፤ ተገ​ኝ​ቶ​አ​ልና ደስ ይላ​ቸ​ውም ጀመር።


ከአ​ባቱ ብላ​ቴ​ኖ​ችም አን​ዱን ጠርቶ፦ ‘ይህ የም​ሰ​ማው ምን​ድን ነው?’ አለው።


በገ​በያ ተቀ​ም​ጠው ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ጠር​ተው፥ “አቀ​ነ​ቀ​ን​ላ​ችሁ፥ አል​ዘ​ፈ​ና​ች​ሁ​ምም፤ ሙሾም አወ​ጣ​ን​ላ​ችሁ፥ አላ​ለ​ቀ​ሳ​ች​ሁ​ምም የሚ​ሉ​አ​ቸው ልጆ​ችን ይመ​ስ​ላሉ።