ሉቃስ 13:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም መልሶ እንዲህ አለው፥ “አቤቱ አፈር ቈፍሬ በሥሯ እስከ አስታቅፋት፥ ፍግም እስከ አፈስባት ድረስ የዘንድሮን እንኳ ተዋት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እርሱ ግን እንዲህ ሲል መለሰለት፤ ‘ጌታ ሆይ፤ ዙሪያዋን እስክኰተኵትላትና ፍግ እስከማደርግላት ድረስ ለዘንድሮ ብቻ ተዋት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ግን መልሶ፥ ጌታ ሆይ! ዙሪያዋን እስክኰተኩትላትና ፍግ እስካፈስላት ድረስ ይህችን ዓመት ደግሞ ተዋት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አትክልተኛው ግን እንዲህ ሲል መለሰለት፤ ‘ጌታዬ ሆይ! እስቲ ለዚህ ዓመት ደግሞ ተዋት፤ ዙሪያዋን ኰትኲቼ ማዳበሪያ አደርግላታለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ግን መልሶ፦ ጌታ ሆይ፥ ዙሪያዋን እስክኰተኵትላትና ፋንድያ እስካፈስላት ድረስ በዚች ዓመት ደግሞ ተዋት። |
“አቤቱ በፊትህስ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆነ፥ ይህ ሕዝብ አንገተ ደንዳና ነውና ጌታዬ ከእኛ ጋር ይሂድ፤ ጠማማነታችንን፥ ኀጢአታችንንና በደላችንን ይቅር በለን፤ ለአንተም እንሆናለን” አለ።
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ “ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም፥ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አያዘነብልም፤ እነዚህን ሕዝቦች ከፊቴ አባርራቸው፤ ይውጡ።
ለሰውነቴ ጕድጓድን ቈፍረዋል፤ በውኑ በመልካም ፈንታ ክፉ ይመለሳልን? ስለ እነርሱ በመልካም እናገር ዘንድ፥ ቍጣህንም ከእነርሱ ትመልስ ዘንድ በፊትህ እንደ ቆምሁ አስብ።
የእግዚአብሔርም አገልጋዮች ካህናት በወለሉና በምሥዋዑ መካከል እያለቀሱ፥ “አቤቱ! ለሕዝብህ ራራ፤ አሕዛብም ይገዙአቸው ዘንድ ርስትህን ለማላገጫ አሳልፈህ አትስጥ፤ ከአሕዛብም መካከል፦ አምላካቸው ወዴት ነው? ስለ ምን ይላሉ?” ይበሉ።
የወይኑን ጠባቂም፦ “የዚችን በለስ ፍሬ ልወስድ ስመላለስ እነሆ፥ ሦስት ዓመት ነው፤ አላገኘሁም፤ እንግዲህስ ምድራችንን እንዳታቦዝን ቍረጣት” አለው።
ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፤ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሓ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።