ሽማግሌውንና ጎበዙን፥ ድንግሊቱንም፥ ሕፃናቱንና ሴቶቹን፥ ፈጽማችሁ ግደሉ፤ ነገር ግን ምልክቱ ወደ አለበት ሰው ሁሉ አትቅረቡ፤ በመቅደሴም ጀምሩ” አላቸው። በቤቱም አንጻር ባሉ ሽማግሌዎች ጀመሩ።
ሉቃስ 12:47 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጌታውን ፈቃድ ዐውቆ እንደ ፈቃዱ የማይሠራና የማያዘጋጅ የዚያ አገልጋይ ቅጣቱ ብዙ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የጌታውን ፍላጎት እያወቀ የማይዘጋጅና ፈቃዱን የማያደርግ ባሪያ እርሱ ክፉኛ ይገረፋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታውንም ፈቃድ አውቆ ያልተዘጋጀ እንደሱም ፈቃድ ያላደረገ ያ ባርያ እጅግ ይገረፋል አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የጌታውን ፈቃድ እያወቀ ያልተዘጋጀ፥ ወይም የጌታውን ትእዛዝ ያልፈጸመ አገልጋይ በብርቱ ይቀጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጌታውንም ፈቃድ አውቆ ያልተዘጋጀ እንደ ፈቃዱም ያላደረገ ያ ባሪያ እጅግ ይገረፋል |
ሽማግሌውንና ጎበዙን፥ ድንግሊቱንም፥ ሕፃናቱንና ሴቶቹን፥ ፈጽማችሁ ግደሉ፤ ነገር ግን ምልክቱ ወደ አለበት ሰው ሁሉ አትቅረቡ፤ በመቅደሴም ጀምሩ” አላቸው። በቤቱም አንጻር ባሉ ሽማግሌዎች ጀመሩ።
የዚያ አገልጋይ ጌታ ባልጠረጠረው ዕለት፥ ባላወቀውም ሰዓት መጥቶ ከሁለት ይሰነጥቀዋል፤ ዕድሉንም ከማይታመኑ ጋር ያደርገዋል።
የሚክደኝን፥ ቃሌንም የማይቀበለውን ግን የሚፈርድበት አለ፤ እኔ የተናገርሁት ቃል እርሱ በመጨረሻዪቱ ቀን ይፈርድበታል።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “ከሰማይ ካልተሰጠህ በቀር በእኔ ላይ አንዳች ሥልጣን የለህም፤ ስለዚህ ለአንተ አሳልፎ የሰጠኝ ሰው ታላቅ ኀጢኣት አለበት” አለው።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “ዕዉሮችስ ብትሆኑ ኀጢኣት ባልሆነባችሁም ነበር፤ አሁን ግን እናያለን ትላላችሁ፤ አታዩምም፤ ስለዚህም ኀጢኣታችሁ ጸንቶ ይኖራል” አላቸው።
የቀድሞውንስ ያለ ማወቅ ዘመን እግዚአብሔር አሳልፎታል፤ ዛሬ ግን በመላው ዓለም ንስሓ እንዲገቡ ሰውን ሁሉ አዝዞአል።