ሉቃስ 12:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታው በመጣ ጊዜ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው አገልጋይ ብፁዕ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታው ሲመለስ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው ባሪያ እርሱ ምስጉን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታው መጥቶ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው ያ ባርያ ብፁዕ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታው ከሄደበት ሲመለስ ልክ እንደታዘዘው ሲፈጽም የሚያገኘው አገልጋይ እንዴት የተባረከ ነው! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታው መጥቶ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው ያ ባሪያ ብፁዕ ነው። |
ይህን የሚያደርግ በእርሱም ጸንቶ የሚኖር፥ ሰንበታትንም የሚጠብቅና የማያረክስ፥ እጁንም ክፋት ከማድረግ የሚጠብቅ ሰው ብፁዕ ነው።”
ጌታቸው በመጣ ጊዜ እንዲህ ሲያደርጉና ሲተጉ የሚያገኛቸው አገልጋዮች ብፁዓን ናቸው፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ወገቡን ታጥቆ በማዕድ ያስቀምጣቸዋል፤ እየተመላለሰም ያገለግላቸዋል።
ጌታችንም እንዲህ አለው፥ “ምግባቸውን በየጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተሰቡ ላይ የሚሾመው ደግ ታማኝና ብልህ መጋቢ ማን ይሆን?