Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሉቃስ 12:43 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 ጌታው መጥቶ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው ያ ባርያ ብፁዕ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 ጌታው ሲመለስ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው ባሪያ እርሱ ምስጉን ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 ጌታው ከሄደበት ሲመለስ ልክ እንደታዘዘው ሲፈጽም የሚያገኘው አገልጋይ እንዴት የተባረከ ነው!

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 ጌታው በመጣ ጊዜ እን​ዲህ ሲያ​ደ​ርግ የሚ​ያ​ገ​ኘው አገ​ል​ጋይ ብፁዕ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 ጌታው መጥቶ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው ያ ባሪያ ብፁዕ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 12:43
8 Referencias Cruzadas  

ከእኔ ጋር ይኖሩ ዘንድ ዐይኖቼ በምድር ምእመናን ላይ ናቸው፥ በቀና መንገድ የሚሄድ እርሱ ያገለግለኛል።


በለሱን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል፥ ጌታውንም የሚጠብቅ ይከብራል።


ይህን የሚያደርግ ሰው ይህንንም የሚይዝ የሰው ልጅ፥ እንዳያረክሰው ሰንበትንም የሚጠብቅ እጁንም ክፋት ከማድረግ የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።


ጌታው ሲመጣ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው ያ ባርያ የተባረከ ነው፤


ጌታቸው በመጣ ጊዜ ሲተጉ የሚያገኛቸው እነዚያ ባርያዎች ብፁዓን ናቸው፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ታጥቆ በማዕድ ያስቀምጣቸዋል፤ ቀርቦም ያገለግላቸዋል።


ጌታም አለ “እንኪያስ ምግባቸውን በጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተ ሰዎቹ ላይ የሚሾመው ታማኝና ልባም መጋቢ ማን ነው?


እውነት እላችኋለሁ፤ ባለው ሁሉ ላይ ይሾመዋል።


ስለዚህ ወዳጆች ሆይ! ይህን ሁሉ እየተጠባበቃችሁ፥ ጌታ ያለ ነውር ወይም ያለ ነቀፋ ሆናችሁ በሰላም እንዲያገኛችሁ በትጋት ኑሩ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos