ወደ ሜዳም በወጡ ጊዜ እንዲህ አሉት፥ “ራስህን አድን፤ ወደ ኋላም አትመልከት፤ አንተንም መከራ እንዳታገኝህ በዚች ሀገር በዳርቻዋና በተራራዋ አትቁም።”
ሉቃስ 12:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፍስ ከምግብ ትበልጣለችና፤ ሰውነትም ከልብስ ይበልጣልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕይወት ከምግብ፣ ሰውነትም ከልብስ ይበልጣልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ ይበልጣልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከምግብ ሕይወት፥ ከልብስም ሰውነት ይበልጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ ይበልጣልና። |
ወደ ሜዳም በወጡ ጊዜ እንዲህ አሉት፥ “ራስህን አድን፤ ወደ ኋላም አትመልከት፤ አንተንም መከራ እንዳታገኝህ በዚች ሀገር በዳርቻዋና በተራራዋ አትቁም።”
እግዚአብሔርም ሰይጣንን፥ “እነሆ፥ ለእርሱ ያለውን ሁሉ በእጅህ ሰጠሁህ፥ ነገር ግን በእርሱ ላይ እጅህን አትዘርጋ” አለው። ሰይጣንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጣ።
ለደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አላቸው፥ “ስለዚህ እላችህዋለሁ፤ ለነፍሳችሁ ስለምትበሉትና ስለምትጠጡት፥ ለሰውነታችሁም ስለምትለብሱት አትጨነቁ።
የማይዘሩትንና የማያጭዱትን፥ ጎተራና ጕድጓድ የሌላቸውን የቍራዎችን ጫጭቶች ተመልከቱ፤ እግዚአብሔር ግን ይመግባቸዋል፤ እንግዲህ እናንተ ከወፎች እንዴት እጅግ አትበልጡም?