የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮሣፍጥን፥ “እግዚአብሔርን የምንጠይቅበት የይምላ ልጅ ሚክያስ የሚባል አንድ ሰው አለ፤ ነገር ግን ክፉ እንጂ መልካም አይናገርልኝምና እጠላዋለሁ” አለው። የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥም፥ “ንጉሥ እንዲህ አይበል” አለ።
ሉቃስ 11:45 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሕግ ዐዋቂዎችም አንዱ መልሶ፥ “መምህር ሆይ፥ ይህን ስትል እኛን እኮ መስደብህ ነው” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሕግ ዐዋቂዎች አንዱ መልሶ “መምህር ሆይ፤ እንዲህ ስትናገር እኮ እኛንም መስደብህ ነው” ሲል መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሕግ አዋቂዎችም አንዱ መልሶ፦ “መምህር ሆይ! ይህን ስትል እኮ እኛን ደግሞ መስደብህ ነው፤” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሕግ መምህራኑም አንዱ ኢየሱስን፥ “መምህር ሆይ፥ ይህንን ስትል እኛንም መስደብህ ነው!” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሕግ አዋቂዎችም አንዱ መልሶ፦ መምህር ሆይ፥ ይህን ማለትህ እኛን ደግሞ መስደብህ ነው አለው። |
የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮሣፍጥን፥ “እግዚአብሔርን የምንጠይቅበት የይምላ ልጅ ሚክያስ የሚባል አንድ ሰው አለ፤ ነገር ግን ክፉ እንጂ መልካም አይናገርልኝምና እጠላዋለሁ” አለው። የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥም፥ “ንጉሥ እንዲህ አይበል” አለ።
ይሰሙኝስ ዘንድ ለማን እናገራለሁ? ለማንስ አዳኛለሁ? እነሆ፥ ጆሮአቸው ያልተገረዘች ናት፤ ለመስማትም አይችሉም፤ እነሆ፥ የእግዚአብሔር ቃል ለስድብ ሆኖባቸዋል፥ ይሰሙት ዘንድ አልፈቀዱምና።
እርሱም እንዲህ አለው፤ “ለእናንተ ለሕግ ዐዋቂዎች ወዮላችሁ! ሰውን ከባድ ሸክም ታሸክሙታላችሁ፤ እናንተ ግን ያን ሸክም በአንዲት ጣታችሁ እንኳን አትነኩትም።
እናንተ ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ወዮላችሁ! የጽድቅንና የዕውቀትን መክፈቻ ወስዳችሁ ትሰውራላችሁና፤ እናንተም አትገቡምና፤ የሚገቡትንም መግባትን ትከለክሉአቸዋላችሁ።”