ይበላም ዘንድ እንጀራን አቀረቡለት፤ እርሱ ግን “ነገሬን እስክናገር ደረስ አልበላም” አለ። እነርሱም “ተናገር” አሉት።
ሉቃስ 10:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከረጢትም፥ ስልቻም፥ ጫማም፥ ምንም ምን አትያዙ፤ በመንገድም ማንንም ሰላም አትበሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኰረጆ ወይም ከረጢት ወይም ጫማ አትያዙ፤ በመንገድ ላይም ለማንም ሰላምታ አትስጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቦርሳም ከረጢትም ጫማም አትያዙ፤ በመንገድ ላይ ለማንም ሰላምታን አትስጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለመንገዳችሁ ምንም አትያዙ፤ የገንዘብ ቦርሳም ቢሆን፥ ከረጢትም ቢሆን፥ ጫማም ቢሆን አትያዙ፤ ከሰው ጋር ሰላምታ በመለዋወጥ በመንገድ ላይ ቆማችሁ ጊዜ አታጥፉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኮረጆም ከረጢትም ጫማም አትያዙ፤ በመንገድም ለማንም እጅ አትንሡ። |
ይበላም ዘንድ እንጀራን አቀረቡለት፤ እርሱ ግን “ነገሬን እስክናገር ደረስ አልበላም” አለ። እነርሱም “ተናገር” አሉት።
አህያውንም አስጭና ሎሌዋን፥ “ንዳ፥ ሂድ፤ እኔ ሳላዝዝህ አታዘግየኝ፤ ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ቄርሜሎስ ተራራ እንሂድ” አለችው።
ኤልሳዕም ግያዝን፥ “ወገብህን ታጠቅ፤ በትሬንም በእጅህ ይዘህ ሂድ፤ ሰውም ብታገኝ ሰላም አትበል፤ እርሱም ሰላም ቢልህ አትመልስለት፤ በትሬንም በሕፃኑ ፊት ላይ አኑር” አለው።
ደግሞም፥ “ያለ ስልቻ፥ ያለ ከረጢትና ያለ ጫማ በላክኋችሁ ጊዜ በውኑ የተቸገራችሁት ነገር ነበርን?” አላቸው፤ እነርሱም፥ “የለም” አሉት።
ዳዊትም አቤሜሌክን፥ “የንጉሥ ጉዳይ ስላስቸኰለኝ ሰይፌንና መሣሪያዬን አላመጣሁምና በአንተ ዘንድ ጦር ወይም ሰይፍ እንዳለ እይልኝ” አለው።