ኤልሳዕም ዳግመኛ ወደ ጌልጌላ ተመለሰ፤ በምድርም ላይ ራብ ነበረ፤ የነቢያትም ልጆች በፊቱ ተቀምጠው ነበር፤ ኤልሳዕም ሎሌውን፥ “ታላቁን ምንቸት ጣድ፤ ለነቢያትም ልጆች ቅጠላ ቅጠል አብስልላቸው” አለው።
ሉቃስ 10:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማርያም የምትባል እኅትም ነበረቻት፤ እርስዋም ከጌታችን ኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጣ ትምህርቱን ትሰማ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም ማርያም የተባለች እኅት ነበረቻት፤ ማርያምም ቃሉን እየሰማች በጌታ እግር ሥር ተቀምጣ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእርሷም ማርያም የምትባል እኅት ነበረቻት፤ እርሷም ደግሞ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጣ ቃሉን ትሰማ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋ ማርያም የምትባል እኅት ነበረቻት፤ ይህች ማርያም በኢየሱስ እግር ሥር ተቀምጣ ትምህርቱን ታደምጥ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእርስዋም ማርያም የምትባል እኅት ነበረቻት፥ እርስዋም ደግሞ ቃሉን ልትሰማ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጣ ነበረች። |
ኤልሳዕም ዳግመኛ ወደ ጌልጌላ ተመለሰ፤ በምድርም ላይ ራብ ነበረ፤ የነቢያትም ልጆች በፊቱ ተቀምጠው ነበር፤ ኤልሳዕም ሎሌውን፥ “ታላቁን ምንቸት ጣድ፤ ለነቢያትም ልጆች ቅጠላ ቅጠል አብስልላቸው” አለው።
ሰዎችም የሆነውን ያዩ ዘንድ ወጡ፤ ሄደውም ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ በደረሱ ጊዜ አጋንንት የወጡለትን ያን ሰው አእምሮዉ ተመልሶለት ልብሱን ለብሶ፥ ከጌታችን ከኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጦ አገኙትና ፈሩ።
ማርያም ግን ዋጋዉ የከበረና የበዛ አንድ ነጥር የጥሩ ናርዶስ ሽቱ ወሰደችና የጌታችን ኢየሱስን እግር ቀባችው፤ በፀጕሯም አሸችው፤ የዚያ ሽቱ መዓዛም ቤቱን መላው።
ጳውሎስም እንዲህ አላቸው፥ “እኔ አይሁዳዊ ሰው ነኝ፤ የቂልቅያ ክፍል በምትሆን በጠርሴስ ከተማ ተወለድሁ፤ በዚችም ከተማ ከገማልያል እግር ሥር ሆኜ አደግሁ፤ የአባቶችንም ሕግ ተማርሁ፤ እናንተ ሁላችሁ ዛሬ እንደምታደርጉትም ለእግዚአብሔር ቀናተኛ ነበርሁ።