እርሱም በመንገድ ሲወጣ አንድ ሰው ወደ እርሱ ሮጦ ተንበረከከለትና “ቸር መምህር ሆይ! የዘላለም ሕይወትን እወርስ ዘንድ ምን ላድርግ?” ብሎ ጠየቀው።
ሉቃስ 10:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህ በኋላ አንድ ሕግ ዐዋቂ ሊፈትነው ተነሣና፥ “መምህር ሆይ፥ የዘለዓለም ሕይወትን እወርስ ዘንድ ምን ላድርግ?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆም አንድ ቀን፣ አንድ ሕግ ዐዋቂ ኢየሱስን ሊፈትነው ተነሥቶ፣ “መምህር ሆይ፤ የዘላለምን ሕይወት ለመውረስ ምን ላድርግ?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆም፥ አንድ ሕግ አዋቂ ተነሥቶ ሊፈትነው እንዲህ አለ፦ “መምህር ሆይ! የዘለዓለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ቀን አንድ የሕግ መምህር ወደ ኢየሱስ መጣ፤ ሊፈትነውም ፈልጎ “መምህር ሆይ! የዘለዓለምን ሕይወት ለማግኘት ምን ማድረግ ይገባኛል?” ሲል ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆም፥ አንድ ሕግ አዋቂ ሊፈትነው ተነሥቶ፦ መምህር ሆይ፥ የዘላለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ? አለው። |
እርሱም በመንገድ ሲወጣ አንድ ሰው ወደ እርሱ ሮጦ ተንበረከከለትና “ቸር መምህር ሆይ! የዘላለም ሕይወትን እወርስ ዘንድ ምን ላድርግ?” ብሎ ጠየቀው።
ብዙ ነቢያትና ነገሥታት እናንተ የምታዩትን ሊያዩ ተመኙ፤ አላዩምም፤ እናንተ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ተመኙ፥ አልሰሙም።”
መውረስ የኦሪትን ሕግ በመሥራት ከሆነ እንግዲህ በሰጠው ተስፋ አይደለማ፤ እነሆ እግዚአብሔር አስቀድሞ ለአብርሃም ተስፋውን ሰጠው።