ሉቃስ 1:47 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልቡናዬም በአምላኬ በመድኀኒቴ ሐሤት ታደርጋለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንፈሴም በመድኀኒቴ በእግዚአብሔር ደስ ትሠኛለች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ትደሰታለች፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤ |
አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፣ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፣ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፣ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫንይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።
ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኀይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን።