አሮንም ሙሴን ተናገረው እንዲህም አለው፥ “እነሆ፥ ዛሬ የኀጢአታቸውን መሥዋዕት፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕታቸውን በእግዚአብሔር ፊት በለዩ ጊዜ፥ ይህች አገኘችኝ፤ ዛሬም የኀጢአቱን መሥዋዕት እበላ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት መልካም አይደለም።”
ዘሌዋውያን 9:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሮንም ወደ መሠዊያው ቀርቦ ስለ ራሱ ኀጢአት መሥዋዕት የሆነውን ጥጃ አረደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሮንም ወደ መሠዊያው መጥቶ ስለ ራሱ የኀጢአት መሥዋዕት የቀረበውን እንቦሳ ዐረደው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሮንም ወደ መሠዊያው ቀርቦ ስለ ራሱ ኃጢአት መሥዋዕት የሆነውን እምቦሳ አረደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሮንም ወደ መሠዊያው ሄዶ መጀመሪያ ስለ ራሱ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርበውን ጥጃ ዐረደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሮንም ወደ መሠዊያው ቀርቦ ስለ ራሱ ኃጢአት መሥዋዕት የሆነውን እምቦሳ አረደ። |
አሮንም ሙሴን ተናገረው እንዲህም አለው፥ “እነሆ፥ ዛሬ የኀጢአታቸውን መሥዋዕት፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕታቸውን በእግዚአብሔር ፊት በለዩ ጊዜ፥ ይህች አገኘችኝ፤ ዛሬም የኀጢአቱን መሥዋዕት እበላ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት መልካም አይደለም።”
እጁንም በኀጢአት መሥዋዕት ራስ ላይ ይጭናል፤ ለሚቃጠልም መሥዋዕት እንስሳትን በሚያርዱበት ስፍራ የኀጢአት መሥዋዕት ፍየልዋን ያርዳታል።