አሮንም ሙሴን ተናገረው እንዲህም አለው፥ “እነሆ፥ ዛሬ የኀጢአታቸውን መሥዋዕት፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕታቸውን በእግዚአብሔር ፊት በለዩ ጊዜ፥ ይህች አገኘችኝ፤ ዛሬም የኀጢአቱን መሥዋዕት እበላ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት መልካም አይደለም።”
ዘሌዋውያን 9:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አረደ፤ የአሮንም ልጆች ደሙን አመጡለት፤ እርሱም በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ረጨው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ አሮን የሚቃጠለውን መሥዋዕት ዐረደ፤ ልጆቹ ደሙን አቀበሉት፤ እርሱም ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ረጨ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አረደ፤ የአሮንም ልጆች ደሙን አመጡለት፥ እርሱም በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ረጨው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርበውንም እንስሳ ዐረደ፤ ልጆቹም ደሙን ወደ እርሱ አመጡለት፤ እርሱም ደሙን በመሠዊያው ጐን በአራቱም ማእዘን ረጨ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አረደ፤ የአሮንም ልጆች ደሙን አመጡለት፥ እርሱም በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ረጨው። |
አሮንም ሙሴን ተናገረው እንዲህም አለው፥ “እነሆ፥ ዛሬ የኀጢአታቸውን መሥዋዕት፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕታቸውን በእግዚአብሔር ፊት በለዩ ጊዜ፥ ይህች አገኘችኝ፤ ዛሬም የኀጢአቱን መሥዋዕት እበላ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት መልካም አይደለም።”
የአሮንም ልጆች ደሙን አቀረቡለት፤ ጣቱንም በደሙ ውስጥ ነክሮ የመሠዊያውን ቀንዶች ቀባ፤ ደሙንም ከመሠዊያው በታች አፈሰሰው።
ክርስቶስ እንደ ወደዳችሁ፥ ራሱንም ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ የሚሆን መሥዋዕትና ቍርባን አድርጎ እንደ ሰጠላችሁ በፍቅር ተመላለሱ።