ዘሌዋውያን 3:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለቍርባኑ የበግ ጠቦትን ቢያቀርብ በእግዚአብሔር ፊት ያቀርበዋል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሥዋዕቱ የበግ ጠቦት ከሆነም፣ በእግዚአብሔር ፊት ያምጣው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለቁርባኑ ጠቦትን ቢያቀርብ በጌታ ፊት ያቀርበዋል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ሰው የሚያቀርበው መባ የበግ ጠቦት ቢሆን፥ በእግዚአብሔር ፊት ያቅርበው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለቍርባኑ ጠቦትን ቢያቀርብ በእግዚአብሔር ፊት ያቀርበዋል፤ |
“ለእግዚአብሔር የሚቀርበው ቍርባን የደኅንነት መሥዋዕት ቢሆን፥ ከላሞች መንጋ ተባት ወይም እንስት ቢያቀርብ፥ ነውር የሌለበትን በእግዚአብሔር ፊት ያቅርብ።
ቍርባኑን ለእግዚአብሔር የሚያቀርብ የኢፍ መስፈሪያ አራተኛ እጅ በሆነ ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ ዐሥረኛ እጅ የሆነ የመልካም ዱቄት መሥዋዕት ያመጣል።
ለመጠጥ ቍርባንም የኢን መስፈሪያ የሆነ መልካም ዱቄት አራተኛ እጅ በሚቃጠለው መሥዋዕት ወይም በእህሉ ቍርባን ላይ ያደርጋል፤ ለእያንዳንዱ ጠቦት ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ያለው መሥዋዕት ይሆን ዘንድ ይህን ያህል ያድርግ።
ክርስቶስ እንደ ወደዳችሁ፥ ራሱንም ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ የሚሆን መሥዋዕትና ቍርባን አድርጎ እንደ ሰጠላችሁ በፍቅር ተመላለሱ።
ነውር የሌለው ሆኖ፥ በዘለዓለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም ሕያው እግዚአብሔርን እናመልከው ዘንድ ሕሊናችንን ከሞት ሥራ እንዴት ይልቅ ያነጻ ይሆን?