ዘሌዋውያን 27:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተሳለውም ሰው ቤቱን ይቤዠው ዘንድ ቢወድድ ከግምቱ ገንዘብ በላይ አምስተኛ እጅ ይጨምር፤ ቤቱም ለእርሱ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤቱን የቀደሰው ሰው መልሶ ሊዋጀው ከፈለገ ግን፣ የዋጋውን አንድ ዐምስተኛ በዋጋው ላይ መጨመር አለበት፤ ቤቱም ዳግመኛ የራሱ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቀደሰውም ሰው ቤቱን ሊቤዠው ቢወድድ በገመትከው የገንዘብ መጠን ላይ አምስት እጅ ይጨምራል፤ ቤቱም ለእርሱ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባለንብረቱ ያንን ቤት መልሶ ለመግዛት ቢፈልግ ግን በዋጋው ላይ በመቶ ሃያ እጅ ይጨምር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀደሰውም ሰው ቤቱን ይቤዠው ዘንድ ቢወድድ ከግምቱ ገንዘብ በላይ አምስተኛ ይጨምር፤ ቤቱም ለእርሱ ይሆናል። |
“ሰውም ለእግዚአብሔር ቅዱስ ይሆን ዘንድ ቤቱን ቢቀድስ፥ ካህኑ መልካም ወይም ክፉ እንደ ሆነ ይገምተዋል፤ ካህኑም እንደሚገምተው መጠን እንዲሁ ይቆማል።
“ሰውም ከርስቱ እርሻ ለእግዚአብሔር ቢሳል፥ እንደ መዘራቱ መጠን ይገመት፤ አንድ የቆሮስ መስፈሪያ ገብስ የሚዘራበት እርሻ አምሳ ወቄት ብር ይገመታል።
የረከሰም እንስሳ ቢሆን እንደ ግምቱ ይቤዠው፤ በእርሱም የዋጋውን አምስተኛ እጅ ይጨምርበታል፤ ባይቤዥም እንደ ግምቱ ይሸጣል።
በተቀደሰ ነገር ላይ ስለ ሠራው ኀጢአት ዕዳ ይከፍላል፤ አምስተኛውንም እጅ ይጨምርበታል፤ ለካህኑም ይሰጠዋል። ካህኑም በበደል መሥዋዕት አውራ በግ ያስተሰርይለታል፤ ኀጢአቱም ይቅር ይባልለታል።