ዘሌዋውያን 26:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ደግሞ አግድሜ በቍጣ እሄድባችኋለሁ፤ ስለ ኀጢአታችሁም ሰባት እጥፍ እበቀላችኋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም ጠላት እሆንባችኋለሁ፤ ስለ ኀጢአታችሁም ሰባት ዕጥፍ አስጨንቃችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም ደግሞ እናንተን በመቃወም እሄዳለሁ፤ እኔም ስለ ኃጢአታችሁ ሰባት እጥፍ እመታችኋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእናንተ ላይ በቊጣ ተመልሼ ካለፈው ሰባት እጥፍ በበረታ ሁኔታ እቀጣችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ደግሞ በእንቢተኝነት እሄድባችኋለሁ፤ ስለ ኃጢአታችሁም ሰባት እጥፍ እመታችኋለሁ። |
ስለዚህ አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ትንቢት ተናገር፤ እጅህን በእጅህ ላይ አጨብጭብ፤ የተገደሉ ሰዎች ሰይፍ ሦስት ጊዜ ይደጋግም፤ ይኸውም የታላቅ ግድያ ሰይፍ ነው፤ ያስደነግጣቸዋልም።
“ከዚያም በኋላ በእንቢተኝነት ብትሄዱብኝ፥ ልትሰሙኝም ባትፈቅዱ እንደ ኀጢአታችሁ መጠን በመቅሠፍት ላይ ሰባት እጥፍ እጨምራለሁ።
እኔም ደግሞ አግድሜ ከእነርሱ ጋር በቍጣ ሄድሁ፤ በጠላቶቻቸውም ምድር አጠፋቸዋለሁ። ነገር ግን በዚያን ጊዜ ያልተገረዘው ልባቸው ያፍራል፤ ስለ ኀጢአታቸውም ይናዘዛሉ፤