የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ሰዎች በዚህ ምድር ቤትንና እርሻን የወይን ቦታንም እንደ ገና ይገዛሉ።”
ዘሌዋውያን 25:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለራሱም ዕዳውን መክፈል ባይችል፥ ሽያጩ በገዛው ሰው እጅ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ይቀመጥ፤ በኢዮቤልዩም ዓመት ይውጣ፤ እርሱም ወደ ርስቱ ይመለስ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ዋጋውን መመለስ ካልቻለ፣ የሸጠው ርስት እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ የገዢው ንብረት ሆኖ ይቈያል፤ በኢዮቤልዩ ዓመት ለባለቤቱ ይመለሳል፤ ሰውየውም ወደ ርስቱ ይመለሳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለማስመለስ ግን በቂ ገንዘብ ባያገኝ፥ ሽያጩ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ በገዛው ሰው እጅ ይሆናል፤ በኢዮቤልዩ ዓመት ነፃ ይወጣል፥ እርሱም ወደ ርስቱ ይመለሳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ለመዋጀት የሚያስችል በቂ ገንዘብ ባይኖረው ርስቱ እስከ ተከታዩ የኢዩቤልዩ ዓመት ድረስ በዚያው በገዛው ሰው እጅ ሊቆይለት ይችላል። በዚያም ዓመት ርስቱ ለባለቤቱ ይመለሳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለራሱም ዕዳውን መክፈል ባይችል፥ ሽያጩ በገዛው ሰው እጅ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ይቀመጥ፤ በኢዮቤልዩ ዓመት ይውጣ፥ እርሱም ወደ ርስቱ ይመለስ። |
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ሰዎች በዚህ ምድር ቤትንና እርሻን የወይን ቦታንም እንደ ገና ይገዛሉ።”
አምሳኛውንም ዓመት ትቀድሳላችሁ፤ በምድሪቱም ለሚኖሩት ሁሉ ነጻነትን ታውጃላችሁ፤ እርሱ ለእናንተ ኢዮቤልዩ ነው፤ ሰው ሁሉ ወደ ርስቱና ወደ ወገኑ ይመለስ።
“ሰውም ቅጥር ባለበት ከተማ መኖርያ ቤትን ቢሸጥ፥ ከተሸጠ በኋላ አንድ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ ለመቤዠት ይችላል፤ ለአንድ ሙሉ ዓመት መቤዠት ይችላል።
አንድ ዓመት እስኪጨረስ ባይቤዠው ቤቱ ለገዡ ይሆናል፤ ቅጥር ባለበት ከተማ ያለውን ያን ቤት ይመረምሩለታል፤ ለገዛው ሰው ለልጅ ልጁ ለዘለዓለም ይጸናለታል፤ በኢዮቤልዩ ዓመትም አይወስዱበትም።