እንዲሁም ኀጢአት እንዳይሆንባቸው፥ እንዳይሞቱም፥ ወደ ምስክሩ ድንኳን ሲገቡ፥ በመቅደሱም ያገለግሉ ዘንድ ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ በአሮንና በልጆቹ ላይ ይሆናል፤ ለእርሱ፥ ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ለዘለዓለም ሥርዐት ይሆናል።
ዘሌዋውያን 22:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቢያረክሱአት እንዳይሞቱ፥ ስለ እርስዋም ኀጢአትን እንዳይሸከሙ፥ ሕግን ይጠብቁ፤ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ካህናት ትእዛዞቼን በመናቅ በደለኛ እንዳይሆኑና እንዳይሞቱ ይጠብቋቸው፤ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባረክሱት ጊዜ እንዳይሞቱ ስለ እርሱም ኃጢአትን እንዳይሸከሙ፥ ትዛዝን ይጠብቁ፤ የምቀድሳቸው እኔ ጌታ ነኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ካህናት ሁሉ እኔ የሰጠኋቸውን የሥርዓት መመሪያዎች ይጠብቁ፤ ይህን ባያደርጉ ግን ለተቀደሱት የትእዛዝ መመሪያዎች ባለመታዘዛቸው በደል ሆኖባቸው ይሞታሉ፤ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቢያረክሱአት እንዳይሞቱ ስለ እርስዋም ኃጢአትን እንዳይሸከሙ፥ ሕግን ይጠብቁ፤ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝ። |
እንዲሁም ኀጢአት እንዳይሆንባቸው፥ እንዳይሞቱም፥ ወደ ምስክሩ ድንኳን ሲገቡ፥ በመቅደሱም ያገለግሉ ዘንድ ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ በአሮንና በልጆቹ ላይ ይሆናል፤ ለእርሱ፥ ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ለዘለዓለም ሥርዐት ይሆናል።
እንዳይሞትም የጢሱ ደመና በምስክሩ ታቦት ላይ ያለውን መክደኛ ይሸፍን ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ዕጣኑን በእሳቱ ላይ ያደርጋል።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “እኔ በስርየቱ መክደኛ ላይ በደመናው ውስጥ እታያለሁና እንዳይሞት በመጋረጃው ውስጥ በምስክሩ ታቦት ላይ ወዳለው ወደ ስርየቱ መክደኛ ወደ ተቀደሰው ስፍራ ሁልጊዜ እንዳይገባ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው።
ስለዚህ ከእናንተ በፊት የነበሩ ሰዎች የሠሩትን ጸያፍ የሆነውን ወግ ሁሉ እንዳትሠሩ፥ በእርሱም እንዳትረክሱ ሥርዐቴን ጠብቁ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና።”
በኀጢአት ሳሉ ከተቀደሰው መሥዋዕት ከበሉ ግን ኀጢአትና በደል ይሆንባቸዋል፤ የማነጻቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝና።”
የመጀመሪያውንም ከእርሱ ባነሣችሁ ጊዜ ስለ እርሱ ኀጢአት አይሆንባችሁም፤ እንዳትሞቱም የእስራኤል ልጆች የቀደሱትን አታርክሱ።”