ዘሌዋውያን 22:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላም፥ ወይም በግ፥ ወይም ፍየል ብትሆን እርስዋንና ልጅዋን በአንድ ቀን አትረዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ላምን ከጥጃዋ፣ በግንም ከግልገሏ ጋራ በአንድ ቀን አትረዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ላም ወይም በግ ብትሆን እርሷንና ልጇን በአንድ ቀን አትረዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ላምን ከጥጃዋ ጋር፥ በግንም ከግልገልዋ ጋር በአንድ ቀን አትረድ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ላም ወይም በግ ብትሆን እርስዋንና ልጅዋን በአንድ ቀን አትረዱ። |
የመጀመሪያውን የምድርህን ፍሬ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ቤት ትወስዳለህ። ጠቦቱን በእናቱ ወተት አትቀቅል።”
የበከተዉን ሁሉ አትብሉ፤ ይበላው ዘንድ በሀገርህ ደጅ ለተቀመጠ መጻተኛ ወይም ለባዕድ ስጠው፤ አንተ ለአምላካህ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሕዝብ ነህና፥ የፍየሉን ጠቦት በእናቱ ወተት አትቀቅል።