ዘሌዋውያን 22:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ |
“የእስራኤል ልጆች ለእኔ ከሚቀድሱአቸው ከቅዱሳን ነገሮች ራሳቸውን እንዲለዩ፥ የተቀደሰውንም ስሜን እንዳያረክሱ ለአሮንና ለልጆቹ ንገራቸው፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
“ሰው ቢዘነጋ፥ ሳያውቅም ለእግዚአብሔር በተቀደሰው በማናቸውም ነገር ኀጢአትን ቢሠራ፥ ለበደል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ከመንጋዉ ነውር የሌለበትን እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን በብር ሰቅል የተገመተውን አውራ በግ ለበደል መሥዋዕት ያቀርባል።
ይህም ለእናንተ ነው፤ የእስራኤል ልጆች ለስጦታ ያቀረቡትን የመጀመሪያ ቍርባን ሁሉ ለአንተ ከአንተም ጋር ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ የዘለዓለም ሕግ እንዲሆን ሰጥቼሃለሁ፤ በቤትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብላው።