ዘሌዋውያን 20:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፊታችሁ በማወጣቸው ሕዝብ ሕግ አትሂዱ፤ ይህን ሁሉ አድርገዋልና ተጸየፍኋቸው አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከፊታችሁ የማሳድዳቸውን አሕዛብ ልማድ አትከተሉ፤ እነዚህን ሁሉ በማድረጋቸው ተጸየፍኋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ከፊታችሁ በማሳድደው ሕዝብ በሆነው ወግ አትሂዱ፤ እነዚህን ሁሉ ነገሮች አድርገዋልና ተጸየፍኋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በፊታችሁ የማባርራቸውን ሕዝቦች ልማድ አትከተሉ፤ ይህን ሁሉ ነገር ስላደረጉ ተጸየፍኳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፊታችሁ በምጥላቸውም ሕዝብ ወግ አትሂዱ፤ ይህን ሁሉ አድርገዋልና ተጸየፍኋቸው። |
እንደ ተቀመጣችሁባት እንደ ግብፅ ምድር ሥራ አትሥሩ፤ እኔም ወደ እርስዋ እንደማገባችሁ እንደ ከነዓን ምድር ሥራ አትሥሩ፤ በሥርዐታቸውም አትሂዱ።
ስለዚህ ከእናንተ በፊት የነበሩ ሰዎች የሠሩትን ጸያፍ የሆነውን ወግ ሁሉ እንዳትሠሩ፥ በእርሱም እንዳትረክሱ ሥርዐቴን ጠብቁ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና።”
ምድራቸውን ትወርሳት ዘንድ የምትገባው ስለ ጽድቅህና ስለ ልብህ ቅንነት አይደለም፤ ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ከፊትህ በሚያጠፋቸው በእነዚያ አሕዛብ ኀጢአት ምክንያትና ለአባቶችህ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም የማለላቸውን ቃል ያጸና ዘንድ ነው።