እንበረምም የአባቱን ወንድም ልጅ ዮካብድን አገባ፤ አሮንንና ሙሴን፥ እኅታቸውንም ማርያምን ወለደችለት፤ የእንበረምም የሕይወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው።
ዘሌዋውያን 20:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአባትህን ወይም የእናትህን እኅት ኀፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ ይህን የሚያደርግ የዘመድን ኀፍረተ ሥጋ ገልጦአል፤ ኀጢአታቸውን ይሸከማሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ከእናትህም ሆነ ከአባትህ እኅት ጋራ ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ ይህ የሥጋ ዝምድናን ማቃለል ስለ ሆነ ሁለታችሁም ትጠየቁበታላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአባትህን ወይም የእናትህን እኅት ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ ይህን የሚያደርግ የዘመዱን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአል፤ በደላቸውን ይሸከማሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአክስትህ ጋር ፍትወታዊ ግንኙነት አታድርግ፤ በዚህ የሥጋ ዝምድናን ማፍረሳቸው ስለ ሆነ ሁለቱም ፍዳቸውን ይቀበላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአባትህን ወይም የእናትህን እኅት ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ ይህን የሚያደርግ የዘመድን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአል፤ ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ። |
እንበረምም የአባቱን ወንድም ልጅ ዮካብድን አገባ፤ አሮንንና ሙሴን፥ እኅታቸውንም ማርያምን ወለደችለት፤ የእንበረምም የሕይወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው።
“ከእናንተም ማንም ሰው ኀፍረተ ሥጋውን ይገልጥ ዘንድ ወደ ሥጋ ዘመዱ ሁሉ አይቅረብ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።