ዘሌዋውያን 2:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም ከተፈተገው እህል፥ ከዘይቱም ወስዶ ከዕጣኑ ጋር መታሰቢያውን ያቀርባል፤ ይህም ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑም ከተፈተገው እህልና ከዘይቱ ወስዶ፣ ከዕጣኑ ሁሉ ጋራ ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ መታሰቢያ አድርጎ ያቃጥል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም ከተፈተገው እህል ከዘይቱም ወስዶ፥ ከዕጣኑ ሁሉ ጋር መታሰቢያውን ያቃጥላል፤ ይህ ለጌታ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን ነው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑም ከዚያ መባ ከፊሉን ወስዶ ለእግዚአብሔር የቀረበ መሆኑን ለማስታወስ ዘይቱንም፥ ዕጣኑንም በሙሉ ከእህሉ ጋር አብሮ ያቃጥለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም ከተፈተገው እህል ከዘይቱም ወስዶ ከዕጣኑ ሁሉ ጋር መታሰቢያውን ያቃጥላል፤ ይህ ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን ነው። |
የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን፥ ለታሰሩትም መፈታትን፥ ለዕውራንም ማየትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።
የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥባሉ፤ ካህኑም ሁሉን የሚቃጠል መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ በጎ መዓዛ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ያቀርበዋል።
እነዚህንም ዐሥራት አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር ታቀርባላችሁ፤ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ለበጎ መዓዛ በመሠዊያው ላይ አይቀርቡም።
“ከመጀመሪያው እህልህ መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ብታቀርብ በእሳት የተጠበሰና የተፈተገ የእህል እሸት ታቀርባለህ።
ካህኑም ከቍርባኑ መታሰቢያውን ይወስዳል፤ በመሠዊያውም ላይ ይጨምረዋል። ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ያለው የሚቃጠል ቍርባን ነው።
እርሱም ሥጋ ለብሶ በዚህ ዓለም በነበረበት ጊዜ፥ በታላቅ ጩኸትና እንባ ከሞት ሊያድነው ወደሚችለው ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፤ ጽድቁንም ሰማው።