ከአባትህ የተወለደችውን የአባትህን ሚስት ልጅ ኀፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ ከአባትህ የተወለደች እኅትህ ናት፤ ኀፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ።
ዘሌዋውያን 18:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የወንድ ልጅህን ሴት ልጅ ኀፍረተ ሥጋ ወይም የሴት ልጅህን ሴት ልጅ ኀፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የአንተ ኀፍረተ ሥጋ ነውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ከወንድ ልጅህ ሴት ልጅ ወይም ከሴት ልጅህ ሴት ልጅ ጋራ ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ ይህ አንተን ያዋርዳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወንድ ልጅህን ሴት ልጅ ኃፍረተ ሥጋዋን ወይም የሴት ልጅህን ሴት ልጅ ኃፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ፤ የእነርሱ ኃፍረተ ሥጋ የአንተ ኃፍረተ ሥጋ ነውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኀፍረተ እንዳይሆንብህ ከልጅ ልጅህ ጋር ፍትወታዊ ግንኙነት አታድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወንድ ልጅህን ሴት ልጅ ኃፍረተ ሥጋዋን ወይም የሴት ልጅህን ሴት ልጅ ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የአንተ ኃፍረተ ሥጋ ነውና። |
ከአባትህ የተወለደችውን የአባትህን ሚስት ልጅ ኀፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ ከአባትህ የተወለደች እኅትህ ናት፤ ኀፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ።
የእኅትህን ኀፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የአባትህ ልጅ ወይም የእናትህ ልጅ በቤት ወይም በውጭ የተወለደች ብትሆን፥ ኀፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ።