የእንበረም ልጆች አሮንና ሙሴ ነበሩ፤ አሮንም ለቅድስተ ቅዱሳን የተቀደሰ ይሆን ዘንድ ተመረጠ፤ እርሱና ልጆቹ ለዘለዓለም በእግዚአብሔር ፊት ያጥኑና ያገለግሉ ነበር፤ በስሙም ለዘለዓለም ይባርኩ ነበር።
ዘሌዋውያን 17:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለአሮንና ለልጆቹ፥ ለእስራኤልም ልጆች ሁሉ እንዲህ ብለህ ንገር፦ እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው፤ እንዲህም አለ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለአሮንና ለልጆቹ፣ ለእስራኤላውያንም ሁሉ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለአሮንና ለልጆቹ ለእስራኤልም ልጆች ሁሉ ተናገር እንዲህም በላቸው፦ ጌታ ያዘዘው ቃል ይህ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ ‘እግዚአብሔር ያዘዘው ትእዛዝ ይህ ነው’ ብለህ ለአሮንና ለልጆቹ እንዲሁም ለእስራኤላውያን ሁሉ ንገር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአሮንና ለልጆቹ ለእስራኤልም ልጆች ሁሉ እንዲህ ብለህ ንገር፦ እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው፥ እንዲህም አለ፦ |
የእንበረም ልጆች አሮንና ሙሴ ነበሩ፤ አሮንም ለቅድስተ ቅዱሳን የተቀደሰ ይሆን ዘንድ ተመረጠ፤ እርሱና ልጆቹ ለዘለዓለም በእግዚአብሔር ፊት ያጥኑና ያገለግሉ ነበር፤ በስሙም ለዘለዓለም ይባርኩ ነበር።
ከእስራኤል ቤት ከመካከላቸውም ከሚኖሩ እንግዶች ማናቸውም ሰው በሬ፥ ወይም በግ፥ ወይም ፍየል ቢያርድ፥ በሰፈሩ ውስጥ ወይም ከሰፈሩ ውጭ ቢያርደው፥