ዘሌዋውያን 16:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍየሉም ኀጢአታቸውን ሁሉ ወደ በረሃ ይሸከማል፤ ፍየሉንም ዛፍ በሌለበት በምድረ በዳ ውስጥ ይለቅቀዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍየሉም ኀጢአታቸውን ሁሉ ተሸክሞ ወደ ምድረ በዳ ይሄዳል፤ ሰውየውም ፍየሉን ሰው ሊኖርበት በማይችል ስፍራ ይልቀቀው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍየሉም በደላቸውን ሁሉ በረሀ ወደ ሆነ ስፍራ ይሸከማል፤ ፍየሉንም በምድረ በዳ ውስጥ እንዲሄድ ይለቅቀዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍየሉንም ኃጢአታቸውን ሁሉ ተሸክሞ ምንም ሰው ወደማይኖርበት ምድረ በዳ ወስዶ ይለቀዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍየሉም ኃጢአታቸውን ሁሉ ወደ በረሀ ይሸከማል፤ ፍየሉንም በምድረ በዳ ውስጥ ይለቅቀዋል። |
“አንተም በግራ ጎንህ ተኛ፤ በምትተኛበትም ቀን ቍጥር የእስራኤልን ቤት ኀጢአት አኑርባት፤ ኀጢአታቸውንም ትሸከማለህ።
አሮንም ሁለቱን እጆቹን በደኅነኛው ፍየል ራስ ላይ ይጭናል፤ በላዩም የእስራኤልን ልጆች በደል ሁሉ፥ መተላለፋቸውን ሁሉ፥ ኀጢአታቸውንም ሁሉ ያስተሰርያል፤ በፍየሉም ራስ ላይ ያሸክመዋል፤ በተዘጋጀው ሰውም እጅ ወደ ምድረ በዳ ይሰድደዋል።
“አሮንም ወደ ምስክሩ ድንኳን ይገባል፤ ወደ መቅደሱም በገባ ጊዜ የለበሰውን የተልባ እግር ልብስ ያወልቃል፤ በዚያም ይተወዋል።
በማግሥቱም ዮሐንስ ወደ እርሱ ሲመጣ ጌታችን ኢየሱስን አይቶ እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ የዓለሙን ኀጢኣት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።
እኛንስ ክርስቶስ ስለ እኛ የኦሪትን መርገም በመሸከሙ ከኦሪት መርገም ዋጅቶናል፤ መጽሐፍ እንዲህ ብሎአልና፥ “በእንጨት ላይ የተሰቀለ ሁሉ ርጉም ነው።”
እንዲሁ ክርስቶስም የብዙዎችን ኀጢአት ያስተሰርይ ዘንድ ራሱን አንድ ጊዜ ሠዋ፤ በኋላ ግን ያድናቸው ዘንድ ተስፋ ለሚያደርጉት ያለ ኀጢአት ይገለጥላቸዋል።