“በስምንተኛው ቀን ነውር የሌለባቸውን፥ ዓመት የሞላቸውን ሁለት ተባት የበግ ጠቦቶች፥ ነውር የሌለባትንም አንዲት የዓመት እንስት የበግ ጠቦት፥ ስለ እህልም ቍርባን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ የሆነ፥ በዘይት የተለወሰ መልካም የስንዴ ዱቄት፥ አንድ ማሰሮ ዘይትም ይወስዳል።
ዘሌዋውያን 14:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚያነጻውም ካህን እነዚህን ነገሮች፥ የሚነጻውንም ሰው በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በእግዚአብሔር ፊት ያቀርባቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውየው የነጻ መሆኑን የሚያስታውቀው ካህን የሚነጻውን ሰውና መሥዋዕቶቹን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ በእግዚአብሔር ፊት ያቅርብ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚያነጻውም ካህን የሚነጻውን ሰውና እነዚህን ነገሮች በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በጌታ ፊት ያኖራቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑም ሰውየውን ካመጣቸው ከእነዚህ ሁሉ መባዎች ጋር ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ወስዶ በእግዚአብሔር ፊት ያቀርባል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚያነጻውም ካህን እነዚህን ነገሮች የሚነጻውንም ሰው በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በእግዚአብሔር ፊት ያኖራቸዋል። |
“በስምንተኛው ቀን ነውር የሌለባቸውን፥ ዓመት የሞላቸውን ሁለት ተባት የበግ ጠቦቶች፥ ነውር የሌለባትንም አንዲት የዓመት እንስት የበግ ጠቦት፥ ስለ እህልም ቍርባን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ የሆነ፥ በዘይት የተለወሰ መልካም የስንዴ ዱቄት፥ አንድ ማሰሮ ዘይትም ይወስዳል።
ካህኑም አንዱን ጠቦት ወስዶ ስለ በደል መሥዋዕት ያቀርባል፤ ያንም አንድ ማሰሮ ዘይት ስለ ልዩ ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ይለየዋል።
ሌዋውያንም ከኀጢአት ራሳቸውን አነጹ፤ ልብሳቸውንም አጠቡ፤ አሮንም ስጦታ አድርጎ በእግዚአብሔር ፊት አቀረባቸው፤ አሮንም ያነጻቸው ዘንድ አስተሰረየላቸው።