“የለምጽ ደዌ በሰው ላይ ቢወጣ እርሱ ወደ ካህኑ ይሄዳል።
“ማንኛውም ሰው ተላላፊ የቈዳ በሽታ ከያዘው፣ ወደ ካህኑ ያምጡት፤
ማናቸውም ሰው በለምጽ ደዌ ቢጠቃ እርሱን ወደ ካህኑ ያመጡታል፤
“ማንም ሰው የሥጋ ደዌ በሽታ ቢይዘው ወደ ካህኑ ያምጡት፤
የለምጽ ደዌ በሰው ውስጥ ቢሆን እርሱን ወደ ካህኑ ያመጡለታል።
ካህኑም ያየዋል፤ እነሆም፥ በቆዳው ላይ ነጭ እባጭ ቢሆን፥ ጠጕሩም ተለውጦ ቢነጣ፥ ሥጋውም በእባጩ ውስጥ ቢያዥ፥
“ሰው በሥጋው ቆዳ ላይ እባጭ ብትወጣበት፥ ብትነጣም፥ በሥጋውም ቆዳ እንደ ለምጽ ደዌ ብትመስል፥ ወደ ካህኑ ወደ አሮን ወይም ከካህናቱ ልጆች ወደ አንዱ ያምጡት።
ካህኑም ያያል፤ እነሆም፥ ምልክቱ በቆዳው ላይ ቢሰፋ ካህኑ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለዋል፤ ለምጽ ነውና።