ዘሌዋውያን 13:47 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የለምጽም ደዌ በልብስ ላይ ቢሆን፥ ልብሱም የበግ ጠጕር ወይም የተልባ እግር ቢሆን፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከበግ ጠጕር ወይም ከበፍታ የተሠራ ማንኛውም ዐይነት ልብስ በተላላፊ በሽታ ቢበከል፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የለምጽም ደዌ በልብስ ላይ ቢወጣ፥ ልብሱም የበግ ጠጉር ወይም በፍታ ቢሆን፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሻጋታ ነገር ከበግ ጠጒር ወይም ከበፍታ በተሠራ ልብስ ቢወጣ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የለምጽም ደዌ በልብስ ላይ ቢሆን፥ ልብሱም የበግ ጠጕር ወይም በፍታ ቢሆን፥ |
ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፤ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ በኀጢአታችን ምክንያት እንደ ቅጠል ረግፈናል፤ እንዲሁም ነፋስ ጠራርጎ ወስዶናል።
ከልብስሽም ወስደሽ በመርፌ የተጠለፉ ጣዖታትን ሠራሽ፤ አመነዘርሽባቸውም፤ ስለዚህ ፈጽመሽ አልገባሽም፤ ከእንግዲህም ወዲህ እንዲህ ያለ ነገር አይሆንም።
ልብሱን ያቃጥላል፤ ድሩ ወይም ማጉ የበግ ጠጕር ወይም የተልባ እግር ቢሆን ወይም ከቆዳ የተደረገ ቢሆን፥ ደዌ ያለበት ሁሉ እየፋገ የሚሄድ ለምጽ ነውና በእሳት ይቃጠላል።
“በበግ ጠጕር ልብስ፥ ወይም በተልባ እግር ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከቆዳ በተደረገ ነገር ላይ ቢሆን፥ ንጹሕ ወይም ርኩስ ያሰኝ ዘንድ የለምጽ ደዌ ሕግ ይህ ነው።”